EconomyEthiopia

ግንባታዎችን የሚያጓትቱ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን የከተማ አስተዳደሩ አስጠነቀቀ።

ግንባታዎችን የሚያጓትቱ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን የከተማ አስተዳደሩ አስጠነቀቀ።

“በተለያየ ምክንያት ግንባታዎችን የሚያጓትቱ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ በኃላ አይታገስም አሉ ኢ/ር ታከለ ኡማ።

ኢ/ር ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች ላይ ለሚሳተፉ የህንፃ ተቋራጭ ባለቤቶች እና አማካሪዎች የስራ መመርያ ሰጥተዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ለብክነት የተጋለጠ እንደነበርም አንስተዋል፡፡
በግንባታ ላይ ያሉ ነባር ፕሮጀክቶችን በተቀመጠላቸዉ ጊዜ ውስጥ የማይጠናቀቁ ከሆነ ውላቸው እንደሚቋረጥ ያሳወቁት ኢ/ር ታከለ ፤በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ የተሰጧቸውን ፕሮጀክቶች ማጠናቀቅ ያልቻሉ እና የህዝብን ሃብት ለከፍተኛ ብክነት እየዳረጉ ያሉ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች በቀጣይነት የከተማ አስተዳደሩ በሚያሰራው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ እንዳይሳተፉ እንደሚደረግም ተናግረዋል ፡፡
እንዲሁም በተለያየ ምክንያት ግንባታዎችን የሚያጓትቱ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ በኃላ እንደማይታገስም አስታውቀዋል፡፡
በመጨረሻም ሁሉም በከተማ አስተዳደሩ የሚገነቡት ግንባታዎች በአስቸኳይ ኦዲት ተደርገው ለከተማ አስተዳደሩ ኮንስትራክሽን ቢሮ ሪፖርት እንዲያደርጉ እና ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ፕሮጀክቶችን ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ እንዲሰሩ መመራያ መስጠታቸውን ከአስተዳደሩ ሰምተናል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button