Breaking News

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተቋማቱ ሀላፊዎች  እና ተወካዮች ጋር በዘርፉ ማሻሻያዎች ዙሪያ ነው የተወያዩት ፡፡

ውይይቱ የተደረገው ዘርፉ  ብቁ ተፎካካሪ እንዲሆን እና ኢኮኖሚን ለማሳደግ ያለውን ሚና ለማጠናከር ነው ተብሏል፡፡

ውይይቱ እስካሁን በፋይናሱ ዘርፍ በተደረጉት ለውጦች፣ የፖሊሲ እና የአስተዳደር ችግሮችን መለየት እና ኃላፊነቶች ግልፅ ማድረግ  ላይ ያተኮረ እንደነበርም ተጠቁሟል፡፡

የመንግስት ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ ዘርፉ የሚጫወተውን ሚና በተመለከተም ተወያይተዋል፡፡

ከዘርፉ ሞያተኞች ጋር የተደረገው ውይይት ለአገር አቀፍ የመንግስት የልማት ፕሮጀክቶች ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ በመስማማት  ተጠናቋል፡፡ መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ነው፡፡

 

leave a reply