EthiopiaSportSports

ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን የቦርድ አባላት ምርጫ ተካሂዶ ም/ፕሬዝዳንት ሆና በሙሉ ድምፅ ተመርጣለች።

የIAAF ወኪል ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል

የIAAF ወኪል ሚ/ር ጂ ኢሥራም ዛሬ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቢሮ በመገኘት የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝታቸው ወቅት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፣ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች በአጠቃላይ የተቋሙ እንቅስቃሴ ገልፃ ተደርጓል። በገለፃው ሚ/ር ጂ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በተያያዘ መረጃ…

ከቀናት በፊት የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ኮንግረስ ስብሰባ በአዲስ አበባ ጥር 4/2011 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ተካሂዷል።

በዕለቱ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን የቦርድ አባላት ምርጫ ተካሂዶ ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ ም/ፕሬዝዳንት ሆና በሙሉ ድምፅ ተመርጣለች።

በተጨማሪም ኮሎኔል ደራርቱ በአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን /CAA/ ውስጥ ሪጅኑን በመወከል የቦርድ አባል ሆና ተመርጣለች።

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button