EthiopiaSocial

በሀገራችን ሰዉ ሲዋሽ ምነዉ  በቅሎ ወለደች አልክ ይባላል፡፡ አሁን ግን እዉነት ነዉ በቅሎ ወልዳለች ፡፡

በሀገራችን ሰዉ ሲዋሽ ምነዉ  በቅሎ ወለደች አልክ ይባላል፡፡

አሁን ግን እዉነት ነዉ በቅሎ ወልዳለች ፡፡

ሰሞኑን ከሰሜን ሸዋ ጣርማ በር ወረዳ የተሰማው ዜና አንዲት በቅሎ ባለተለመደ ሁኔታ አምሳያዋን መውለዷን ነዉ።

የጣርማ በር ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው በመዘዞ ንኡስ ወረዳ ኮሶበር ቀበሌ መጋቢት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ለሊት ላይ አንዲት በቅሎ አምሳያዋን ግልገል በመውለድ ብዙዎችን አስደንቃለች።

የጽህፈት ቤቱ ተወካይ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ አለማየሁ ለኢዜአ እንደገለጹት በቅሎዋ የወለደችው ባልተለመደ ሁኔታ ነው።

በአካባቢው በርከት ያለ በቅሎ ቢኖርም ከእዚህ ቀደም እንዲዚህ አይነት ክስተት ተከስቶ እንደማያውቅ ተናግረዋል፡፡

የበቅሎ ባለቤት አቶ ሙላት ኃይለሚካኤል በበኩላቸው በቅሎዋን በ2009 ዓ.ም ገዝተው ሲገለገሉባት መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

” የበቅሎዋ ሰውነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወፈረ መምጣቱንና ጡቶቿ ማጋታቸውን ብመለከትም እርግዝና ይሆናል ብዬ አልገመትኩም” ብለዋል።

በበቅሎዋ መውለድ መገረማቸውን የገለጹት አቶ ሙላት፣ የተወለደችው ሴት ግልገል በአሁኑ ወቅት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡

እናትየዋም የወለደቻትን ግልገል በማጥባት ላይ መሆኗን ተናግረዋል፡፡

በጣርማ በር ወረዳ እንስሳት ሃብት ጽህፈት ቤት የእንስሳት ጤና ባለሙያ አቶ ዘላላም ደምሴ በበኩላቸው አህያ ከፈረስ ጋር ተዳቅላ በቅሎ ስትወልድ ማየት የተለመደ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

“በኮሶበር ቀበሌ ሰሞኑን የሆነው ክስተት ግን ከእዚህ እውነታ የተለየና ያልተለመደ ነው” ብለዋል።

በቅሎ በዘር እራሷን መተካት እንደማትችል ቢታወቅም እንዲህ አይነት ክስተት ከአንድ ሚሊዮን በቅሎዎች መካከል በአንዷ ላይ ሊከሰት እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button