Uncategorized

የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከጦርነት ይልቅ ጉርብትናችንን እናጠናክር እያሉ ነው

የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከጦርነት ይልቅ ጉርብትናችንን እናጠናክር እያሉ ነው

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ ጃቫድ ዛሪፍ ጎረቤት ሀገራት ጠንካራ ወደጅነት መፍጠር የሚሹ ከሆነ፤ ከጦር መሳሪያ ክምችት ፉክክር ይልቅ ውይይትን ሊያስቀድሙ ይገባል ብለዋል፡፡

ዛሪፍ ይህን  ያሉት በኢራቅ መዲና ባግዳድ ለተሰባሰቡ በመቶዎች ለሚቆጠሩ የኢራን እና ኢራቅ የቢዝነስ ተቋማትን ወክለው ለተገኙ ግለሰቦች ነው፡፡

ጃቫድ ዛሪፍ በንግግራቸው ጠንካራ ቀጠና ለመፍጠር ውይይት  የጦርነትን ቦታ ሊተካ ይገባል፤ ትብብር ከግጭት ይቀድማል፤ ወንድማዊ ግንኙነት ደግሞ በውጭ ዜጎች መካከል መተማመንን ይፈጥራል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ዛሪፍ አፅንኦት ሰጥተው እንደገለፁት በጠንካራ ቀጠና ግንባታ ሂደት ውስጥ ወደፊት ለሚታየው ተስፋ ሁሉም ሀገራት አንዱ በአንዱ ላይ እምነት ሊያሳድሩ ይገባል ነው ያሉት፡፡

እንደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሀሳብ ይህንን ግብ ዳር ለማድረስ ሀገራቸው ከሁሉም ጎረቤት ሀገራት ለሚመጡ ወዳጅነት ፈላጊዎች እና ከኢራቅ ለሚመጡ የትብብር እና ልማት ስራዎች ያለምንም ገደብ እጇን ዘርግታ ታስተናግዳለች ፡፡

‹‹ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በተደረገው ትግል በርካታ የኢራን እና ኢራቅ ወጣቶች ደም ፈስሷል እናም በሁለቱ ሀገራት ዜጎች መካከል ያለው ጥልቅ ትስስር መሀል ገብቶ ጥል ለመፍጠር የሚፈተፍት የትኛውም ኃይል አቅም የለውም›› ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በዚህ የንግድ ስብሰባ የሁለቱን ሀገራት የግል ዘርፍ  ወኪሎች ያገናኘ ሲሆን የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በእርሳቸው የሚመራ ልኡክ፣ በባግዳድ የኢራን አምባሳደር ኢራጅ ማስጅድ እና ስድስት የኢራቅ ሚኒስትሮችም ታድመውታል፡፡

እንደ ፕሬስ ቴሌቪዥን ዘገባ የስብሰባው ዋና ዓላማ በኢራቅ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ በሚቻልባቸው ዘርፎች ለመምከር እና የንግድ ትብብርን ለማሳደግ ነው ተብሏል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button