EthiopiaNewsPolitics

ኢትዮጵያዊያን አምባሳደሮች አመታዊ  ጉባኤያቸውን እያካሄዱ ነው ፡፡

ኢትዮጵያዊያን አምባሳደሮች አመታዊ  ጉባኤያቸውን እያካሄዱ ነው ፡፡

ኢትዮጵያን በውጭ የሚወክሉ አምባሳደሮች ቆንስላ ጄኔራሎች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳይሬክተር ጄኔራሎች የሚሳተፉበት ጉባኤ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነው፡፡

ጉባኤው  በዋናነት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት  እና በውጭ የሚገኙ ሚሲዮኖች የስራ እንቅስቃሴ ፣የሚያጋጥሙ  ችግሮች እና መፍትሄዎቸቻው ላይ ያተኩራል ተብሏል፡፡

ሌላው የውይይቱ አጀንዳ ክልላዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች በኢትዮጵያ እና በጎረቤት አገራት ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖ ላይ የሚመክር ነው።

እንደውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ገለፃ ስብሰበው በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ፣ በዜጎችና በዳያስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮች ላይም ትኩረት ያደርጋል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ውቅት በተለያዩ የውጭ አገራት 46 ኤምባሲዎችና 14 ቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤቶችን ከፍታ  እየሰራች ትገኛለች።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close