AfricaNewsPolitics

ሎረን ባግቦ ከተከሰሱበት የጦር ወንጀል ነፃ ተባሉ

ሎረን ባግቦ ከተከሰሱበት የጦር ወንጀል ነፃ ተባሉ

ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የቀድሞውን የአይቮሪ ኮስት ፕሬዝዳንት ሎረን ባግቦን በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ የሚያስብል ማስረጃ ባለመግኘቱ በነፃ እዲለቀቁ ወስኗል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው አቃቤ ህግ ተከሳሹን ጥፋተኛ የሚያስብል ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ ነው ፍርድ ቤቱ ባግቦ በፍጥነት ከእስር እንዲለቁ ትእዛዝ የሰጠው፡፡

ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ጋር ክስ የተመሰረተባቸውን ወጣቱን ፖለቲከኛ ቻርለስ ብሌ ጎዴንም በተመሳሳይ መልኩ ፍርድ ቤቱ በነፃ አስናብቷቸዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ባግቦ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት በዜጎች ላይ ኢሰብዓዊ ድርጊት ፈጽመዋል በሚል አራት ተደራራቢ ክሶች ነበር የተመሰረተባቸው፡፡

ይሁን እንጂ ባግቦ  ከተከሰሱባቸው አራት የወንጀል ድርጊቶች መካከል በአንዱም ጥፋተኛ ሆነው ባለመገኘታቸው ነው ፍርድ ቤቱ በነፃ እነዲፈቱ የወሰነው፡፡

ተከሳሹ ባግቦ የፍርድ ሂደታቸው ከሁለት ዓመት በላይ የፈጀ ሲሆን  ጠበቃቸ ባለፈው ህዳር ወር ደንበኛየ ያለ አግባብ  ፍትህ እየተነፈጉ ነው የሚል አቤቱታ አቅርበው ነበር፡፡

በቀድሞዎቹ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንቶች ሎረን ባግቦ እና አላሳኒ ኦታራ መካከል በተፈጠረው  የስልጣን ሽሚያ ግጭት ተቀስቅሶ ከ3 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button