EthiopiaPolitics

በመንግሥት የታቀደው ፕራይቬታዜሽንና የኢኮኖሚ ሪፎርም የሚመራበት ፍኖተ ካርታ ፀድቆ ተግባራዊ መሆን ጀመረ፡፡

በመንግሥት የታቀደው ፕራይቬታዜሽንና የኢኮኖሚ ሪፎርም የሚመራበት ፍኖተ ካርታ ፀድቆ ተግባራዊ መሆን ጀመረ፡፡

በመንግሥት የተያዙ ግዙፍ ኩባንያዎችን በሙሉና በከፊል ወደ ግል ይዞታ እንዲዘዋወሩ ለማድረግና አጠቃላይ የኢኮኖሚ ሪፎርም ለማከናወን የተያዘው ዕቅድ የሚመራበት ፍኖተ ካርታ፣ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩ ታወቋል።

አንድ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ፍኖተ ካርታው ፀድቆ ወደ ሥራ ከተገባ ከሁለት ወራት በላይ አስቆጥሯል።

ፍኖተ ካርታው መንግሥት በእጁ የሚገኙ ግዙፍ ኩባንያዎች በሽያጭ ወደ ግል ይዞታ የሚተላለፉበትን መሠረታዊ ማዕቀፎችና ሂደቶች የነደፈ ሲሆን፣ መንግሥት ካቀደው አጠቃላይ የኢኮኖሚ ሪፎርም ጋር ተጣጥሞ መፈጸም እንዳለበት የታሰበ መሆኑንም ኃላፊው አስረድተዋል።

የፀደቀው መሪ ዕቅድ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ ኮሚቴ የበላይነት እንዲፈጸም መወሰኑንና ለዚህ አማካሪ ኮሚቴ ተጠሪ የሆነ ዓብይ ኮሚቴ በገንዘብ ሚኒስትሩ እንደሚመራ ያስቀምጣል።

የትግበራ እንቅስቃሴው ከተጀመረ በኋላ መውጣት ይገባቸዋል ተብለው የተለዩ የሕግ ማዕቀፎች መኖራቸውን የገለጹት ኃላፊው፣ የቴሌኮም አገልግሎት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ሕግና የኢንቨስትመንት አዋጅን ማሻሻልና የመንግሥት ኢንተርፕራይዞች አዋጅ ይገኝበታል ብለዋል።

የቴሌኮም ኤጀንሲው ሥልጣን የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ለሚፈልጉ ኩባንያዎች የንግድ ፈቃድ መስጠትና መቆጣጠር ሲሆን፣ በመንግሥት ዕቅድ መሠረት ከሦስት ዓመት በኋላ ከኢትዮ ቴሌኮም በተጨማሪ ሌሎች የቴሌኮም አገልግሎት ለሚሰጡ የግል ኩባንያዎች ፈቃድ መስጠት ሊጀመር እንደሚችል ጠቁመዋል።

የኢንቨስትመንት ሕጉን በማሻሻል ለውጭ ኩባንያዎች ዝግ የተደረጉ ዘርፎችን ክፍት በማድረግና ውድድር በማስፈን፣ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን ለማፋጠን  መታቀዱም ታዉቋል።

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button