Breaking News

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ሊካሄድ ነው

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ሊካሄድ ነው

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ሊካሄድ ነው

ከኢህአዴግ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የዘንድሮው የወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ከጥር 19 እስከ ጥር 21 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ ይሆናል።

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የአዘጋጅ ኮሚቴው ቃል አቀባይ ጫላ ኦሊቃ የጉባኤውን ዝግጅት አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፥ ጉባዔው ከእናት ድርጅቱ ጉባኤ ማግስትና ሀገሪቱ በሁለንተናዊ የለውጥ እንቅስቀሴ ባለችበት ወቅት የሚካሄድ መሆኑን ተናግሯል።

ጉባኤውን ለማካሄድ የሚያስችል ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ የአራቱ ብሄራዊ ድርጅቶች የሊግ ተወካዮችና ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ይካሄዳል።

ጉባኤው በ3ኛው መደበኛ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎችን መነሻ በማድረግና አፈጻጸማቸውን በመገምገም፥ ጥንካሬዎች የሚጎለብቱበትና እጥረቶች የሚታረሙበት አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል፡፡

ከዚህ ባለፈም በአባል ሊጎች ደረጃ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎችን በማጠናከርና በማቀናጀት በሊጉ ውስጥ ዴሞክራሲያዊነትን በሚያሰፋና የሊጉን ተቋማዊ አቅም በሚያጠናክር መልኩ ይካሄዳልም ነው የተባለው።

ሊጉ ከመቸውም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ በመውጣት በወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲሁም በስብዕና ግንባታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ውጤታማ ስራ መስራት የሚያስችሉትን አቅጣጫዎች እንደሚያስቀምጥም ነው የሚጠበቀው።

የኦዲፒ ወጣቶች ሊግ ነገ እንደሚጀር ሰምተናል፡፡

 

leave a reply