Breaking News

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሶስት ግጥሚያዎች ይከናወናሉ

በትግራይ ስታዲዬም መቐለ 70 እንደርታ ኢትዮጵያ ቡናን ያስተናግዳል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሶስት ግጥሚያዎች ይከናወናሉ

የ12ኛ ሳምንት የሊጉ መርሀግብር ዛሬ በሶስት ግጥሚያዎች ሲጀመር፤ ሀዋሳ ላይ ሲዳማ ቡና ከ መከላከያ ይጫወታሉ፡፡

በትግራይ ስታዲዬም መቐለ 70 እንደርታ ኢትዮጵያ ቡናን ያስተናግዳል፤ ሽረ ላይ ደግሞ ስሑል ሽረ ከ ድሬዳዋ ከነማ ይፋለማሉ፡፡

በነገው ዕለት እንዲሁ ሶስት ጨዋታዎች ሲከናወኑ፤ በሳምንቱ ተጠባቂ ግጥሚያ በአማራ ክልል ደርቢ ባህር ዳር ከነማ በግዙፉ ባህር ዳር ስታዲዬም ፋሲል ከነማን ያስተናግዳል፡፡

በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲዬም አዳማ ከነማ ከ  ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፤ ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከነማ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ከሚገኘው ደቡብ ፖሊስ ጋር በደቡብ ደርቢ ይገናኛሉ፡፡

ሀሙስ ወላይታ ድቻ ወደ ጅማ አቅንቶ ከጅማ አባ ጅፋር ጋር ጅማ ስታዲዬም ላይ ይጫወታሉ፡፡

ክልል ላይ የሚከናወኑት ሁሉም ግጥሚያዎች በተመሳሳይ 9፡00 የሚደረጉ ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ በውጤት ማጣት ቀውስ ውስጥ የሚገኘውን ደደቢት ያስተናዳል፡፡

ሊጉን ኢትዮጵያ ቡና በ22 ነጥብ ይመረዋል፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በ18 ይከተላል፤ ፋሲል ከነማ በተመሳሳይ 18 ነጥብ በግብ ክፍያ አንሶ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ ሀዋሳ እና ሲዳማ ቡና በ17 ነጥቦች አራተኛና አምስተኛ ደረጃ ላይ ተሰይመዋል፡፡

ጅማ አባ ጅፋር፣ ደቡብ ፖሊስ እና ደደቢት ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ፡፡

leave a reply