EthiopiaPolitics

የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት ያዘጋጀው የእርቀ ሰላም መድረክ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

 

የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት ያዘጋጀው የእርቀ ሰላም መድረክ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ ላይም የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተሳተፉ ነው።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት ሰብሳቢ አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ፥ “ሀገራችንን የምንጠብቀው እኛ ነን፤ የሀገራችን ጉዳይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አይደለም፤ የእኛ ጉዳይ ነው፤ ሁላችንንም ስለ ሀገራችን ሰላም ያገባናል” ብለዋል።

“ጦርነት አንፈልግም፤ ህዝባችን በሰላም ወጥቶ መግባት ይፈልጋል” ያሉት አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ፥ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ እርስ በእርስ መጋጨት ትተው ችግራቸውን በውይይት እንዲፈቱም ጠይቀዋል።

የኦሮሞ አባ ገዳዎች እና ሀደ ሲቄዎች በአንድነት በመቆም በፓርቲዎቹ መካከል እርቅ እንዲሰፍን የጠየቁ ሲሆን፥ “ፓርቲዎቹ የቀረበላቸውን ጥያቄ እስኪቀበሉ ድረስ አንቀመጥም ወደ ቤትም አንሄድም” ሲሉ ጠይቀዋል።

ፋና እንደዘገበዉ የፖለቲካ ፓርቲዎቹም በአንድነት በመሆን ከኦሮሞ አባ ገዳዎች እና ሀደ ሲቄዎች የቀረበላቸውን የሰላም እና የእርቅ ስምምነት መቀበላቸውን አስታውቀዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button