PoliticsWorld

ጣሊያን እና ፈረንሳይ በአፍሪካ ጉዳይ እየተነታረኩ ነው::

ጣሊያን እና ፈረንሳይ በአፍሪካ ጉዳይ እየተነታረኩ ነው::

የቀድሞዎቹ ጥብቅ ወዳጆች ፈረንሳይ እና ጣሊያን በመካከላቸው ያለው ግንኙነት ነፋስ ገብቶበታል የሚለው ወሬ በስፋት እየተሰማ ነው፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው ይህ ነገር የተፈጠረው ባለፈው ዓመት በጣሊያን አዲስ የጥምር መንግስት ከተመሰረተ ጀምሮ ነው፡፡

ፈረንሳይ በአፍሪካ የምታራምደውን ፖሊሲ የአንድ ወገን ተጠቃሚነትን አጉልቶ የሚያሳይ ነው ስትል ጣሊያን ትከሳለች፡፡

የኢማኑኤል ማክሮን አስተዳደር በሊቢያ ሰላም እንዲሰፍን ፍላጎት የለውም  ምክንያቱም ሀገሪቱ ሰላም ከሆነች የነዳጅ ዘይት ፍላጎቷን ማሟላት አትችልም በማለትም መከራከሪያዋን ታቀርባለች፡፡

የፈረንሳይ መንግስት በበኩሉ ፓሪስ የሚገኙትን የጣልያን አምባሳደር ጠርቶ ከሮም የተሰነዘረበትን ወቀሳ እንዲያብራሩለት እስከመጠየቅ ደርሷል፡፡

የጣሊያን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር  ሉዊጂ ዲ ማዮ ፈረንሳይ በአፍሪካ ድህነት እንዲስፋፋ እና ዜጎቿ በጅምላ ወደ አውሮፓ እንዲሰደዱ መንገዱን ታመቻቻለች ብለዋል፡፡

ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ቤተ መንግስት የወጣ መረጃ ግን ጣሊያን ለፈረንሳይ እና ለጀርመን ክብር የማትሰጠው የአውሮፓ ህብረት እንዲጠናከር ባለን አቋም እንጂ ለአፍሪካዊያን ተቆርቁረው አይደለም የሚል ነው፡፡

የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ምንም እንኳን ፖለቲካዊ አለመግባባቶች ቢፈጠሩም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት አያበላሸውም በማት ነገሩን ለማለዘብ ሲሞክሩ ተደምጠዋል፡፡

ገለልተኛ የሆኑ ወገኖች ግን ጣሊያንም ሆነች ፈረንሳይ የአፍሪካ በተለይ የሊቢያ ጉዳይ  የሚያጣላቸው የጥቅም ግጭት ነው በማለት አስተያየታቸውን ይሰጣሉ፡፡

 

 

መንገሻ ዓለሙ

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close