EthiopiaPolitics

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከቢል ጌትስ ጋር ተወያይተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከቢል ጌትስ ጋር ተወያይተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዳቮስ የዓለም ኢኮኖሚ ጉባኤ ጎን ለጎን ከተለያዩ አካላት ጋር ተወያይተዋል።

በዚህም ከቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ተባባሪ ሊቀመንበር ከሆኑት ቢል ጌትስ ጋር ተገናኝተው የተወያዩ ሲሆን ፋውንዴሽኑ በኢትዮጵያ በጤና፣ በግብርና፣ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ዘርፎች ላይ ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩና ቢል ጌትስ በግብርና መስኖና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ለመተባበር ተስማምተዋል::

በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከአሊባባ ሊቀመንበር ጃክ ማ ጋር ተገናኝተው ገንቢ ውይይት አድርገዋል። ሁለቱ ወገኖች ምጡቅ የቴክኖሎጂ እድገት በገበያ እና ማህበረሰብ ላይ የሚያመጡትን ለውጥ በተመለከተ ተወያይተዋል ተብሏል።

ጃክ ማ በኢትዮጵያ ውስጥ የህዝቦችን የዕለት ተዕለት ህይወት በሚጠቅም መልኩ የቴክኖሎጂ ከተማዎች ልማት መስክ ሀብት ለማፍስስ ያሉ አማራጮችን ለመለየት ተስማምተዋልም ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሲውዘርላንድ ዳቮስ  የነበራቸውን የአውሮፓ ቆይታ በተሳካ ሁኔታ አጠናቀዉ ወደ ቤልጅየም ብራስልስ ማቅናታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃውን አድርሶናል::

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button