Breaking News

በጂግጂጋ ከተማ በሚከበረው የከተሞች ፎረም ላይ ማንኛውም ተሳታፊ የጸጥታ ሥጋት ሊያድርበት እንደማይገባ ክልሉ አስታወቀ፡፡

በጂግጂጋ ከተማ በሚከበረው የከተሞች ፎረም ላይ ማንኛውም ተሳታፊ የጸጥታ ሥጋት ሊያድርበት እንደማይገባ ክልሉ አስታወቀ፡፡

በጂግጂጋ ከተማ በሚከበረው የከተሞች ፎረም ላይ ማንኛውም ተሳታፊ የጸጥታ ሥጋት ሊያድርበት እንደማይገባ ክልሉ አስታወቀ፡፡

8ኛው የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ ከየካቲት 9 እስከ 14 ድረስ ‹‹መደመር ለኢትዮጵያ ከተሞች ብልጽግና›› በሚል መሪ ቃል ይከበራል።

ፎረሙን አስመልክቶ በሰሰጠው መግለጫ የከተሞች ፎረም አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢና የፌዴራል ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚንስትር ዴኤታ አቶ ካሣሁን ጎፌ፤ የከተሞች ፎረም መከበር ዋና አላማው የከተማ ነዋሪዎችን፣ የመንግስትና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ትብብር በማጠናከር የከተሞች ልማት እንዲፋጠን ማስቻል ነው ብለዋል፡፡

ሚንስትር ዴኤታው ከተሞች ያላቸውን እምቅ አቅም በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በቱሪዝም፣ በታሪካዊ፣ በባህላዊና በማህበራዊ እሴቶቻቸው ዙሪያ የማስተዋወቅ አጋጣሚን ያሰፋል ሲሉ አክለዋል፡፡

የሶማሌ ክልል የከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አብዱል ፈታህ ሸህ ቢሂ በበኩላቸው፤ ማንኛውም ተሳታፊ በክልሉ የጸጥታ ሁኔታ  ላይ ምንም ዓይነት ሥጋት ሊያድርበት አይገባም ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

ለፎረሙ አስፈላጊው ዝግጅት ከህዝቡ፣ ከጸጥታ መዋቅሩ፣ ከእምነት አባቶችና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር መደረጉን የቢሮ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም መከበር የጀመረው ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን በልማት የተሻሉ ከተሞች እውቅና እና ምስጋና ይቸራቸዋል፡፡ አዳዲሲ የፈጠራ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ይበረታታሉ ፡፡

 

leave a reply