Breaking News

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአውሮፓ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ተመለሱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአውሮፓ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ተመለሱ

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ሚር ዐቢይ አሕመድ የአውሮፓ ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ተመለሱ::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጣሊያን የጀመሩትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ስዊዘርላንድና ቤልጂየምን በማካለል ተጠናቅቋል፡፡

በጉብኝቱም ከተለያዩ አገራት መሪዎችና የቢዝነስ አንቀሳቃሾች ጋር በመምከር የሁትዮሽ ግንኙነትን ከማጠናከር ባለፈ ኢትዮጵያን በኢንቨስትመንትና ማገዝ የሚያስችሉ ስምምነቶች ተፈርመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአውሮፓ ህብረት መቀመጫ በሆነችው ቤልጂየም የነበራውን ጉብኝት ሲያጠናቅቁ በብራስልስ ያለውን የኢትዮጵያን ኢምባሲ ጎብኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአውሮፓ የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀው አዲስ አበባ ዛሬ ማለዳ ገብተዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አመልክቷል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

leave a reply