Politics

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና ኦነግ ተኩስ ለማቆም ተስማሙ። የኦነግ ሠራዊት ትጥቅ ፈትቶ ወደ ካምፕ እንዲገባ ውሳኔ ተላልፏል

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና ኦነግ ተኩስ ለማቆም ተስማሙ። የኦነግ ሠራዊት ትጥቅ ፈትቶ ወደ ካምፕ እንዲገባ ውሳኔ ተላልፏል።

ሁለቱም አካላት ስምምነቱን የፈጸሙት አምቦ ላይ በተካሄደው የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትና የኦነግና የእርቀ ሠላም ጉባዔ ላይ ነው።

በስምምነቱ የኦነግ ሠራዊት በ20 ቀናት ውስጥ ትጥቅ ፈትቶ ወደ ካምፕ እንዲገባ ውሳኔ ተላልፏል።

በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል እርቅ ለማውረድ በአዲስ አበባ በተካሄደው ጉባኤ የተመረጠው 71 አባላት ያሉት የቴክኒክ ኮሚቴ ባሳለፈው ባለ 6 አንቀጽ የውሳኔ ሐሳብ መሰረት ነው በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል ያለው ጦርነት እንዲቆም ውሳኔ የተላለፈው።

በክልሉ ዘላቂ ሠላም ለማስፈንም የኦነግን ሠራዊት በ20 ቀናት ውስጥ ወደ ካምፕ የማስገባት ስራ እንደሚከናወን ኮሚቴው አሳውቋል።

ወደ ካምፕ ለሚገባው የኦነግ ሠራዊት ደማቅ አቀባበል የሚደረግለት ሲሆን በሁለት ወራት የካምፕ ቆይታው የተለያዩ ስልጠናዎችን ይወስዳል ተብሏል።

ከስልጠናው በኋላ እያንዳንዱ አባል እንደ ፍላጎቱ በግል ስራ መሠማራት ወይም ወደ መንግስት የሠላም ማስከበር ኃይል መቀላቀል እንደሚችልም በእርቀሰላም ዝግጅቱ ላይ ተነግሯል።

ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ሁለቱ ፓርቲዎች በሚዲያ ትችትና የአቋም መግለጫ መስጠት እንደማይችሉም ተገልጿል።

በጉባኤው አባ ገዳዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሁለቱ ፓርቲዎች ተወካዮች፣ ምሁራን፣ ሃደ ሲንቄዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የአምቦና አካባቢው ነዋሪዎችና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ የአመራር አባላት ተሳትፈዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button