Social

የሀገር ሽማግሌዎቹ በአፋርና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት ተስማሙ

የሀገር ሽማግሌዎቹ በአፋርና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት ተስማሙ።

ሰሞኑን በአፋርና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ለመፍታት የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች መስማማታቸው ተገለጸ።

በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣  የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በውይይቱም የተፈጠረውን ግጭት  ለመፍታት የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት መሪዎችና የሃገር ሽማግሌዎች መስማማታቸው ነው የተገለፀው።

ከዚህ ባሻገርም   የተፈጠረውን ግጭት  መንስኤ ለማጣራትና ግጭቱ ዳግም እንዳይከሰት ለማድረግ   ከሁለቱ ክልሎች  የተውጣጣ የጋራ ኮሚቴ ተቋቁሟል።

በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ኡስታዝ አቡበክር ሁለቱ ህዝቦች በሃይማኖት በባህል እና በጋብቻ ተሳስረው የኖሩ በመሆናቸው በመካከላቸው መሰል ግጭት መፈጠሩ አግባብ አለመሆኑን ተናግረዋል።

ስለሆነም የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት አባቶችና  የሀገር ሽማግሌዎች በቀጣይ ምንም ዓይነት ግጭት እንዳይከሰት ሰላም ለማውረድ መስማማታቸውን ተናግረዋል።

ስለሆነም  የሃይማኖት አባቶችና  የሀገር ሽማግሌዎች ከስምምነት ባሻገር ወደ ህብረተሰቡ ወርደው ለጋራ  ሰላም መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ዘይኑ ጀማል በበኩላቸው መንግስት በአካባቢው ግጭት ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል ሲል ፋና ዘግቧል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button