Breaking News

በኤሌክትሮኒክስ የተደገፈ ወረቀት አልባ የህክምና ና የጤና መረጃ ሥርዓት ተግባራዊ ሊሆን ነው ተባለ

በኤሌክትሮኒክስ የተደገፈ ወረቀት አልባ የህክምና የጤና መረጃ ሥርዓት ተግባራዊ ሊሆን ነው ተባለ

በኢትዮጵያ  በኤሌክትሮኒክስ የተደገፈ ወረቀት አልባ የህክምና ና የጤና መረጃ ሥርዓት ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የዲጂታይላይዜሽን የጤና አገልግሎት ሥርዓትን ያስተዋወቀበትን መርሐ ግብር በመቀሌ ከተማ ባካሄደበት ወቅት እንዳስታወቀው ሥርዓቱ በሙከራ ደረጃ በትግራይ፣ በአማራ፣በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች በሚገኙ 1ሺህ60 የጤና ተቋማት ላይ ተጀምሯል፡፡

ለዚህ ተግበራ እንዲረዳም በጤና ተቋማቱ የሚሰሩ 2ሺህ 120 የጤና ባለሙያዎች የኮምፒዩተርና የታብሌት ሞባይል አገልገሎት አሰጣጥ ሰልጠና ስራ ጀምረዋል ተብሏል።

ሥርዓቱ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በ34 ሺህ ጤና ኬላዎች በታብሌት ሞባይል ታግዞ ሥራ ላይ እንደሚውልም ተገልጿል።

ሥርዓቱን ለማስጀመር ለመሣሪያዎች መግዣ፣ ለሶፍት ዌር መተግበሪያና ለባለሙያዎች ስልጠና ከ210 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቧል ኢዜአ እንደዘገበው።

 

leave a reply