SportSports

ዛሬ ምሽት በኤፍ ኤ ካፕ አራተኛ ዙር አርሰናል እና ማንችስተር ዩናይትድ ይፋለማሉ

ዛሬ ምሽት በኤፍ ኤ ካፕ አራተኛ ዙር አርሰናል እና ማንችስተር ዩናይትድ ይፋለማሉ

በአራተኛ ዙር የኤምሬት ኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ ዛሬ ማንችስስተር ዩናይትድ ወደ ለንደን አቅንቶ በኤመሬት ስታዲየም ምሽት 4፡55 ሲል ከአርሰናል ጋር ይጫወታል፡፡

በዚህ ግጥሚያ መድፈኞቹ የተከላካዩን ሂክቶር ቤዬሪን ግልጋሎት በጉዳት ምክንያት የማያገኝ ይሆናል፡፡ ሄንሪክ ሚኪታሪያንም ቢሆን ከጉዳቱ ያላገገመ በመሆኑ የቀድሞ ክለቡን አይገጥምም ተብሏል፡፡

አሰልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር  ቺሊያዊው አሌክሲስ ሳንቼዝ ከቋንጃ ጉዳቱ በማገገሙ በዚህ ጨዋታ ይሰለፋል ብሏል፤ ለግብ ጠባቂው ዳቪድ ዴ ሂያ ግን እረፍት እንደሰጠው ተናግሯል፡፡

ማርኮስ ሮሆ እና ፌላይኒ በጉዳት ከጨዋታው ውጭ ናቸው፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በሪስቶል ሲቲ ከቦልተን ዋንደረርስ ይገናኛሉ፡፡

በነገው ዕለት በርካታ ጨዋታዎች ሲከናወኑ ከነዚህም መካከል ምሽት 12፡00 ላይ ማንችስተር ሲቲ ከ በርንሊ፣ ብራይተን ከ ዌስት ብሮሚች አልቢዮን፣ ኒውካስትል ዩናይትድ ከ ዋትፎርድ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ዕሁድ ምሽት 1፡00 ላይ ክሪስታል ፓላስ በሴልህረስት ፓርክ ከ ቶተንሃም እንዲሁም ምሽት 3፡00 ቼልሲ ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ ከሸፊልድ ዌንስዳይ ይገናኛሉ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button