Social

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2019 የአለም አቀፍ አሰላሳዮች  መድረክ ተሸላሚ ሆኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር / አብይ አህመድ 2019 የአለም አቀፍ አሰላሳዮች  መድረክ ተሸላሚ ሆኑ፡፡

የአለም አቀፍ የአሳቢዎች መድረክ (Global Thinkers Forum) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ተሸላሚ ያደረጋቸው ከፍተኛ የሆነ የማሰብ ችሎታቸውን በመጠቀም ሃላፊነታቸውን በብቃት ተወጥተዋል ብሎ ነው።

በ2012 የተመሰረተው ይኸው ለግለሰቦችና መሪዎች እውቅናና ሽልማት የሚሰጠው  አለም አቀፍ የሽልማት ድርጅት በ24 በተለያዩ ዘርፎች በ2019 ተሸላሚ ናቸው ካላቸው ግለሰቦችና መሪዎች መካከል የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አካቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የተሸለሙበት ዘርፍ በመከላከያና ጥበቃ ዘርፍ ሲሆን በዚህ ዘርፍ ከተመረጡት አስር ግለሰቦች መካከል አንዱ ሆነዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ዘርፍ የተመረጡት አንድ አመት ባልሞላ ጊዜ ከጎረቤት ሃገር ኤርትራ ጋር ሰላም በማምጣት ታሪክ በመስራታቸው እንደሆነ የአለም አቀፍ የአሳቢዎች መድረክ (Global Thinkers Forum) ዌብሳይት ላይ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በዚህ መድረክ ባለፉት አስር አመታት ምርጥ አስር ተሸላሚዎች ከሆኑ መሪዎችና ግለሰቦች መካከል የጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ መርክል፤ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እና የአሊባባ መስራች ጃክ ማ ይገኙበታል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button