Ethiopia

ኢትዮጵያ በአመታዊ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ተካፈለች 

ኢትዮጵያ በአመታዊ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ተካፈለች

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የተመራ የኢትዮጵያ መንግስት የልዑካን ቡድን በብራስልስ ቤልጂየም በተካሄደው በአመታዊው የአፍሪካ ህብረትና የአውሮፓ የአውሮፓ ህብረት የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተካፍሏል።

ጉባኤው ላይ የአፍሪካ ህብረት አባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና የአውሮፓ ህብረት አባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተገኙ ሲሆን፣ ስብሰባውን በጋራ የመሩት የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነት እና የሴኪዩሪቲ ፖሊሲ ተወካይ ፌዴሪካ ሞገርኒ እና የሩዋዳው የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሪቻርድ ዚቤራ ናቸው።

ወይዘሮ ሂሩት በአገራችን እየተካሄደ ስላላው ሁሉን አቀፍ የለውጥ ስራ እና የአፍሪካ ቀንድ ክልልን በተመለከተ ገለጻ ሰጥተዋል። በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ለውጥ በሃገሪቱ አዲስ የሰላም ምዕራፍ መክፈቱን፣ በአካባቢው አዲስ ተስፋና መነቃቃትን መፍጠሩንም አብራርተዋል። በኢትዮጵያና በኤርትራ መካካል የተፈጠረው ሰላም በአፍሪካ ቀንድና በክልሉ የሰላም በር መክፈቱን ጨምረው ገልጸዋል።

በልማትና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በሃገሪቱ አስራአምስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች በመገንባት ላይ እንደሆነና ከነዚህ ውስጥ በሰባቶቹ ዓለም አቀፍ ብራንድ ያላቸው ኩባንያዎችን ስራ ለማስጀመር የአንድ መስኮት አገልግሎት መሰጠት መጀመሩን ወይዘሮ ሂሩት ተናግረዋል።

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button