EthiopiaSportSports

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ስሑል ሽረ የመጀመሪያ ሶስት ነጥቡን አሳክቷል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ስሑል ሽረ የመጀመሪያ ሶስት ነጥቡን አሳክቷል

የሊጉ የ13ኛ ሳምንት ቀሪ ሶስት ጨዋታዎች በትናንትናው ዕለት ተከናውነዋል፤ መቐለ ላይ በትግራይ ደርቢ የተገናኙት ሁለቱ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙት ደደቢት እና ስሑል ሽረ ሲሆኑ የሽረው ቡድን በሰዒድ ሁሴን ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 በማሸነፍ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ሶስት ነጥብ ማሳካት ችሏል፡፡ ቡድኑ በ12 የሊጉ መርሀግብሮች 11 ነጥቦች በመሰብሰብ ከነበረበት የወራጅ ቀጠና ውስጥ መውጣት ችሏል፡፡

ሌላኛው ጨዋታ ሶዶ ላይ በወላይታ ድቻ እና በባህር ዳር ከነማ መካከል ተካሂዶ በ1 ለ 1 አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ ባዬ ገዛህኝ ለባለሜዳዎቹ፤ ጃኮ አራፋት ደግሞ ለጣናው ሞገድ ቡድን ከመረብ አገናኝተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየም መከላከያ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ተጫውቶ በተመሳሳየይ በ1 ለ 1 አቻ ውጤት አጠናቅቀዋል፡፡

ሁለቱም ግቦች በፍፁም ቅጣት ምቶች የተገኙ ሲሆን ታፈሰ ሰለሞን ለደቡቡ ቡድን እንዲሁም ምንይሉ ወንድሙ ለጦሩ ቡድን ማስቆጠር ችለዋል፡፡

አንድ ተስተካካይ ግጥሚያ ያላቸው ፈረሰኞቹ ሊጉን በ24 ነጥቦች ይመራሉ፤ የዲዲዬ ጎሜሱ  ቡና በሁለት ነጥብ አንሶ በ22 ይከተላል፤ ሀዋሳ ከተማ በ21 ሶስተኛ ደረጃ እንዲሁም መቐለ 70 እንደርታ፣ ሲዳማ ቡና እና ፋሲል ከነማ በእኩል 20 ነጥቦች በግብ ክፍያ ተበላልጠው ከአራት እስከ ስድስት ያለውን ደረጃ ተቆናጥጠዋል፡፡

መከላከያ፣ ደቡብ ፖሊስና ደደቢት ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙ ቡድኖች ናቸው፡፡

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ዳዋ ሆቴሳ ከአዳማ፣ አዲስ ግደይ ከሲዳማ ቡና እና የሀዋሳው ታፈሰ ሰለሞን በ8 ጎሎች ሲመሩ የመከላከያው ምንይሉ ወንድሙ በ7 ጎል ይከተላል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button