ያለ ህጋዊ ሰነድ ወደ ውጪ ሊወጣ የነበረ የባህር ዛፍ አጠና በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
ምንም ህጋዊ ሰነድ ሳይኖረው እና ግምታዊ ዋጋው 400 ሺህ ብር የሚያወጣ የባህርዛፍ አጠና መያዙን የጅግጅጋ ቅ/ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃው አቶ ተስፋዬ አረጋዊ በተባለ አሽከርካሪ አማካኝነት በሰሌዳ ቁጥር 79780/00054 በሆነ ተሳቢ መኪና ተጭኖ ሊወጣ ሲል ቶጎጫሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በጉምሩክ ባለሙያዎችና በመከላከያ ሰራዊት አባላት የጋራ ጥረት ሊያዝ ችሏል፡፡
በተያያዘም በቀን 20/05/11 ከምሽቱ 3፡30 ላይ አቶ ሙሴ ዘካሪያ የተባለ ተጠርጣሪ 2 ግራም የሚሆን ሜርኩሪ መሰል ማዕድን በሶማሌ ክልል አድርጎ ወደ ሶማሌ ላንድ ሊያስወጣ ሲል በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጅግጅጋ ቅ/ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡
ምንጭ፤-ገቢዎች ሚኒስቴር