SportSports

ኳታር የእስያ ዋንጫ የፍፃሜ ተፋላነቷን አረጋገጠች

ኳታር የእስያ ዋንጫ የፍፃሜ ተፋላነቷን አረጋገጠች

ትናንት የእስያ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ አንድ ጨዋታ ሲከናወን፤ የውድድሩ አዘጋጇ ሀገር የተባበበሩት ኤመሬቶች እና ኳታር ያደረጉት ፍልሚያ በኳታር የ4 ለ 0 አሸናፊነት ተደምድሟል፡፡

በመሀመድ ቢን ዛይድ ስታዲየም ላይ በተካሂደው ጨዋታ  ቦአሌም ኮክሂ፣ አልሞኤዝ አሊ፣ ሃሳን አል ሃይዶስ እና ካሊፋ ሃሚድ ደግሞ ሀገራቸውን ወደ ፍፃሜ ያበቁ ጎሎችን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ኳታርም ለመጀመሪያ ጊዜ ለፍፃሜ ጨዋታ አልፋለች፡፡

በዚህም ለዋንጫ ጨዋታ የኳታር እና ጃፓን ብሄራዊ ቡድኖች በመጭው ዓርብ አቡ ዳቢ ላይ በተገማሸረው የዛይድ ስፖርትስ ሲቲ ስታዲየም ይፋለማሉ፡፡

ከትናንት በስቲያ በሀዛ ቢን ዛይድ ስታዲየም በተካሄደ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ጃፓን ኢራንን 3 ለ 0 በመርታት የፍፃሜ ተፋላሚ መሆኗን ማረጋገጧ ይታወሳል፡፡

እአ.አ በ1956 ዓ/ም በጀመረው ውድድር፤ ጃፓን ለፍፃሜ የደረሰችባቸውን አራት ውድድሮች በሙሉ በማሸነፍ ከአህጉሩ ከፍተኛ ዋንጫ ያገኘች ሀገር ስትሆን እስካሁን በአንድ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ ከመሳተፍ ውጭ ታሪክ የሌላት ኳታር በውድድሩ ካሳየችው አቋም አንፃር ጥሩ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሳውዲ አረቢያና ኢራን ሶስት ጊዜ ያህል ውድድሩን አሸንፈዋል፡፡

በ24 ቡድኖች መካከል የተጀመረው 17ኛው የእስያ ዋንጫ፤ በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች አዘጋጅነት ከጥር 5/2019 ጀምሮ እየተከናወነ ሲሆን በመጪው ዓርብ በይፋ ይጠናቀቃል፡፡

ለኳታር የሚጫወተው ትውልደ ሱዳናዊው አጥቂ አልሞኤዝ አሊ የውድድሩን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት በ8 ጎሎች እየመራ ይገኛል፡፡

የውድድሩ አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን የውድድሩ ዋንጫ እና የአምስት ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ያገኛል፤ የፍፃሜ ተፋላሚው 3 ሚሊየን ፓውንድ እንዲሁም የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚ ቡድኖች የአንድ ሚሊየን ዶላር ሽልማት ይበረክትላቸዋል፡፡ ሁሉም ተሰታፊ 24 ብሔራ ቡድኖች የ200 ሺ ዶላር ያገኛሉ ተብሏል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button