EthiopiaSportSports

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለአማራ እና ትግራይ ክልል እግር ኳስ ቡድኖች እና ደጋፊዎችን አመሰገነ

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለአማራ እና ትግራይ ክልል እግር ኳስ ቡድኖች እና ደጋፊዎችን አመሰገነ

ክለቦቹ እና ደጋፊዎቹ በምስክር ወረቀት የታጀበ ምስጋና የተቸራቸው ባሳዩት ስፖርታዊ ጨዋነት መሆኑን የክልሉ ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ.ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ ለአብመድ በሰጡት ቃል ነው፡፡

አቶ አሰማኽኝ በሁለቱ ክልሎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የሁለቱ እግር ኳስ ቡድች በገለልተኛ ሜዳ እየተጫወቱ ከአንድ ዓመት በላይ መቆየታቸው፤ ለቡድኖቹ የኢኮኖሚ ውድቀት እና ለክልሎቹ ደግሞ የቱሪዝም ፍሰት መሰናክል ሆኗል ብለዋል፡፡

ተፈጥሮ በክለቦቹ መካከል የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት ከበርካታ ባለድርሻ አካላት ጋር ረጅም ጊዜ የወሰደ ስራ እንደተሰራ ያወሱት አቶ አሰማኸኝ የጥሉን ግድግዳ ለሰበሩ ቡድኖች እና ደጋፊዎች በክልሉ መንግስት ስም የምስጋና የምስክር ወረቀት ሰጥተናል ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

ከአንድ ዓመት በላይ ታግዶ የነበረውን የሁለቱ ክልሎችን ቡድኖች አለመግባባት በቀዳሚነት ለሰበረው ለደሴ ከነማ እግር ኳስ ቡድን እና ከደሴ ተከትለው ለገቡ ፋሲል ከነማ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና አክሱም ከነማ እግር ኳስ ቡድን፤ በክልሉ የመንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ.ቤት ዋና ዳይሬክተር ኃላፊ አቶ አሰማኸኝ አስረስ እና በክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ባዘዘው ጫኔ በጋራ የተፈረመበት የምስጋና የምስክር ወረቀት ተልኮላቸዋል፡፡

ስፖርት እና ፖለቲካ የተለያዩ ሜዳዎች ናቸው ያሉት አቶ አሰማኸኝ ስፖርት ከተዝናኖቱ በተጨማሪ ኃገራዊ አንድነት፣ፍቅር ፣መቻቻል እና አብሮነት የሚሰበክበት ሜዳ በመሆኑ ሁሉም ሰው ስፖርትን ከፖለቲካ ለይቶ ማየት እንደሚገባው ጠቁመዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button