Uncategorized

በከተማችን ከሚገኙ 130 ሪል እስቴት አልሚዎች ዉስጥ ስድስቱ ብቻናቸዉ የሚጠበቅባቸዉን ግብር የከፈሉት ተባለ፡፡    

በከተማችን ከሚገኙ 130 ሪል እስቴት አልሚዎች ዉስጥ ስድስቱ ብቻናቸዉ የሚጠበቅባቸዉን ግብር የከፈሉት ተባለ፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር የሬል እስቴት አልሚዎች እና ባለቤቶች ያሉባቸውን ችግሮች በተመለከተ የአስጠናውን ሪፖርት ሲያቀርብ ነዉ ይህንን የገለጸዉ፡፡

ጥናቱ ለባለሀብቶች እና ለመንግስት ባለድርሻ አካላት ይፋ ሲደረግ በከተማችን የሚገኙ 130 የሪል እስቴት  ህንፃ አልሚዎች  አብዛኞቹ ግብር ለመክፈል ቸልተኛ  መሆናቸው ተነግሯል፡

የገቢዎች ሚኒሰቴር  የገቢዎች ጥናት  አጣሪ ኮሚቲ ወ/ሮ ሰብለ ገ/እግዚአብሄር እንዳሉት በከተማችን  ከሚገኙ  130 የሪል ስቴት ህንፃ አልሚዎች  መሀከል  6ቱ  ብቻ የግብር ግዴታቸውን በአግባቡ የተወጡ  ሲሆኑ ቁጥራቸው 21 የሚሆኑት  ደግሞ በተቆራረጠ መልኩ የሚከፍሉ መሆናቸው ተነግሯል፡፡ ቀሪዎቹ 103 ሪል ስቴቶቹ ግን  የግብር ግዴታቸውን እንዳልተወጡ ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም 130 የሚሆኑት የሬል ስቴት አልሚዎች ከያዟቸው  4 ሚሊዮን ካሜ በላይ መሬት መንግስት ማግኝት የሚገባውን ገቢ አጥቷል፡፡

ዘገባዉ የአቢ ፍቃዱ ነዉ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button