AfricaCOVID-19News

ግብፅ በኮሮናቫይረስ ምክንያት 47 ዶክተሮቿን በሞት ማጣቷ ትልቅ ስጋት ሆኖባታል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2 ፣ 2012 ግብፅ በኮሮናቫይረስ ምክንያት 47 ዶክተሮቿን በሞት ማጣቷ ትልቅ ስጋት ሆኖባታል ተባለ::የብግብፅ የህክምና ማህበር በሰጠው መግለጫ የሀገሪቱ የጤና አጠባበቅ ስርዓት በፍጥነት ካልተስተካከለና ለሀኪሞች ልዩ እንክብካቤ ካልተደረገላቸው የበለጠ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ብቻ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሰባት ዶክተሮች መሞታቸው ሁኔታው ምን ያህል አደገኛ እየሆነ መምጣቱን ያሳያል ነው የተባለው፡፡ ከሁለት ሳምንታት በፊት ዋሊድ ያህያ የተባለ ሀኪም በኮቪድ 19 ሲሞት የሚሰራበት ሆስፒታል ምልክቱ እየታየበት ምርመራ እንኳን ሳያደርግለት ቀርቷል በማለት በርካታ ዶክተሮች ተቃውሟውን አሰምተው ነበር፡፡ ዶክተሮቹ ተገቢው ጥበቃ አልተደረገልንም ብለው መናገራቸው በመንግስት በኩል እንዳልተወደደላቸውና ይባስ ብሎ የኮሮናቫይረስ ስረጭትን ለመግታት የተሄደበት መንገድ ትክክል አይደለም ብለው የተከራከሩ ሶስት የሚሆኑ ዶክተሮች መታሰራቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር በዘገባው አመላክቷል፡፡ ግብፅ በአፍሪካ የመጀመሪያዋ የኮሮናቫይረስ የተከሰተባት ሀገር ስትሆን ከ35 ሺህ በላይ ሰዎች
በቫይረሱ ሲያዙባት ከ1 ሺህ በላይ ዜጎቿ ሞተዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button