World News

የቀድሞዋ የአሜሪካ ቀደማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማ ትራምፕ አሜሪካን ከችግር የመታደግ አቅም የላቸውም አሉ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 የቀድሞዋ የአሜሪካ ቀደማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማ ትራምፕ አሜሪካን ከችግር የመታደግ አቅም የላቸውም አሉ:: ቀዳማዊት እመቤቷ ፕሬዚዳንቱ ውጤት ያለው ስራ ሰርቶ ለማሳየት ከበቂ በላይ ጊዜ ተሰጥቷቸዋል ግን አንድም ፍርያማ ተግባር አላከናወኑም ብለዋል፡፡

ትራምፕ ለሀገራችን ትክክለኛው መሪ አይደሉም ያሉት ሚሼል አንድ ቀላል ምሳሌ ብናነሳ የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ በአሜሪካ የተከሰተውን ሁኔታ ማረጋጋት አልቻሉም ብለዋል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ቀዳማዊት እመቤቷ አሜሪካዊያን ከችግር መውጣት ከፈለጉ ትራምፕን ዳግም እንዳይመርጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ አሜሪካዊያን በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሲሰቃዩና በየቀኑ የሚወዷቸውን በሞት ሲነጠቁ እያዩ ምንም የማይመስለው መሪ አያስፈልጋቸውም ሲሉም ትራምፕን አጥብቀው ወቅሰዋል፡፡

ዘሌጎቻቸው የሚጠቅም ስራ ከመስራት ይልቅ የሚተቿቸውን ሁሉ እንደጠላት በመቁጠር በህፃናት ላይ ሳይቀር የሚወሰደውን የሃይል እርምጃም ኮንነዋል ቀዳማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማ፡፡ በአንፃሩ የፓርቲያቸው ተወካይ የሆኑት ጆ ባይደን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ባገለገሉበት ወቅት ያሳዩትን ብቃት በማስታወስ የካበተ ልምድ እንዳላቸውና ቢመረጡ ሀገሪቱን ባአግባቡ መምራት እንደሚችሉ አልጠራጠርም ብለዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button