EducationEthiopia

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  ለ6 ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  ለ6 ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

ዩኒቨርሽቲዉ በትላንትናዉ ዕለት ለዶ/ር ሂሩት ወልደ ማርያምን፣ ለዶ/ር ተፈሪ ገድፍን ፣ ለዶ/ር ምሩፅ ግደይን ፣ ለዶ/ር ሃጎስ አሸናፊን፣ ለዶ/ር መረራ ጉዲናን እና ለዶ/ር ጌታቸው አሰፋን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው 6 መምህራን እነማን ናቸዉ? በአጭሩ እነሆ፤-

 

  1. ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም የመጀመርያ፣ ሁለተኛ እና የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በቋንቋ ጥናት (Linguistics) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል፡፡

ፕሮፌሰሯ  በግላቸውና ከሙያ ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በጥናትና ምርምር የተሰሩ ከ6 በላይ ጥናታዊ ፅሁፎችን በታወቁ ሀገራዊና አለምዓቀፋዊ መፅሄቶች ላይ ለህትመት በማብቃት ከሚጠበቅባቸው 35 የህትመት ነጥብ 42 ነጥብ አስመዝገበዋል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ የዩኒቨርሲቲ ቦታዎች ላይ አገልግሎ የሰጡ ሲሆን ብዙ የማህበረሰብ አገልግሎቶችና የሙያ ነክ አስተዋጽኦ አድርገዋል:: ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሂዩማኒቲስ፣ የቋንቋዎች ጥናት፣ የጆርናሊዝምና የኮሚዩኒኬሽን ኮሌጅ የቋንቋ ጥናት ትምህርት ክፍል ባልደረባ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

  1. ፕሮፌሰር ተፈሪ ገድፍ የመጀመርያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ዲግሪያቸውን በፋርማሲ (Pharmacy) ትምህርት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በፋርማሲ ትምህርት በጀርመን ከማርቲን ሉተር ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል፡፡ ፕሮፌሰር ተፈሪ በግላቸውና ከሙያ ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በጥናትና ምርምር የተሰሩ ከ20 በላይ ጥናታዊ ፅሁፎችን በታወቁ ሀገራዊና አለምዓቀፋዊ መፅሄቶች ላይ ለህትመት በማብቃት ከሚጠበቅባቸው 35 የህትመት ነጥብ 104.56 ነጥብ አስመዝገበዋል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ የዩኒቨርሲቲ ቦታዎች ላይ አገልግሎ የሰጡ ሲሆን ብዙ የማህበረሰብ አገልግሎቶችና የሙያ ነክ አስተዋጽኦ አድርገዋል:: ፕሮፌሰር ተፈሪ ገድፍ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ የፋርማሲ ትምህርት ክፍል መምህር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

 

  1. ፕሮፌሰር ምሩፅ ግደይ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በባዮሎጂ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በባዮዳይቨርሲቲ (Biodiversity) ከSwedish University of Agricultural Sciences፣ እንዲሁም የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ቦታኒካል ሳይንስ (Botanical Science) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል፡፡ ፕሮፌሰር ምሩፅ በግላቸውና ከሙያ ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በጥናትና ምርምር የተሰሩ ከ18 በላይ ጥናታዊ ፅሁፎችን በታወቁ ሀገራዊና አለምዓቀፋዊ መፅሄቶች ላይ ለህትመት በማብቃት ከሚጠበቅባቸው 35 የህትመት ነጥብ 56 ነጥብ አስመዝገበዋል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ የዩኒቨርሲቲ ቦታዎች ላይ አገልግሎ የሰጡ ሲሆን ብዙ የማህበረሰብ አገልግሎቶችና የሙያ ነክ አስተዋጽኦ አድርገዋል:: ፕሮፌሰር ምሩፅ ግደይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአክሊሉ ለማ የፓቶባዮሎጂ ኢንስቲትዩት (Aklilu Lemma Institute of Pathobiology) በእንዶድና ሌሎች የመድሃኒት ዕጽዋት የምርምር ማዕከል (Endod and Other Medicinal Plants Research Unit)ባልደረባ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
  2. ፕሮፌሰር ሃጎስ አሸናፊ የእንስሳት ህክምና ዲግሪያቸውንና የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በቤልጄም ከሉቨን የካቶሊክ ዩኒቨርስቲ(Katholic University of Leuven)አግኝተዋል፡፡ ፕሮፌሰር ሃጎስ በግላቸውና ከሙያ ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በጥናትና ምርምር የተሰሩ ከ24 በላይ ጥናታዊ ፅሁፎችን በታወቁ ሀገራዊና አለምዓቀፋዊ መፅሄቶች ላይ ለህትመት በማብቃት ከሚጠበቅባቸው 35 የህትመት ነጥብ 94.06 ነጥብ አስመዝገበዋል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ የዩኒቨርሲቲ ቦታዎች ላይ አገልግሎ የሰጡ ሲሆን ብዙ የማህበረሰብ አገልግሎቶችና የሙያ ነክ አስተዋጽኦ አድርገዋል:: ፕሮፌሰር ሃጎስ አሸናፊ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በእንስሳት ህክምና እና ግብርና ኮሌጅ የፓቶሎጂና ፓራሲቶሎጂ (Pathology and Parasitology) ትምህርት ክፍል መምህር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
  3. ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በፖለቲካ ሳይንስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከአሜሪካን ዩኒቨርስቲ ኢን ካይሮ (American University in Cairo)፣ እንዲሁም የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በፖለቲካ ሳይንስ ከኢንስቲትዩት ኦፍ ሶሻል ስተዲስ (Institute of Social Studies) አግኝተዋል፡፡ ፕሮፌሰር መረራ በግላቸውና ከሙያ ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በጥናትና ምርምር የተሰሩ ከ12 በላይ ጥናታዊ ፅሁፎችን በታወቁ ሀገራዊና አለምዓቀፋዊ መፅሄቶች ላይ ለህትመት በማብቃት ከሚጠበቅባቸው 35 የህትመት ነጥብ 37.25 ነጥብ አስመዝገበዋል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ የዩኒቨርሲቲ ቦታዎች ላይ አገልግሎ የሰጡ ሲሆን ብዙ የማህበረሰብ አገልግሎቶችና የሙያ ነክ አስተዋጽኦ አድርገዋል:: ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለማአቀፍ ግንኙነት (Political Science and International Relations) ትምህርት ክፍል መምህር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

 

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button