Breaking News

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የደህንነት መኮንኖች ተመረቁ።

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የደህንነት መኮንኖች ተመረቁ

በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የክንፈ ብሄራዊ ደህንነት ጥናት ሰልጣኞች የምረቃ ስነስርዓት የተካሄደው  ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በተገኙበት ነው።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንደተናገሩት ተመራቂ የደህንነት መኮንኖች የኢትዮጵያን የደህንነት ዋስትና ለማረጋገጥ መስራት ይጠበቅባቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ተመራቂዎቹ ታማኝነታቸው ለህዝብና ለሀገር በመሆኑ ኃላፊነታቸውን በከፍተኛ ሙያዊ ብቃት እና ደህንነትን በማስፈን ላይ እንዲያተኩሩ አመላክተዋል።

በመቀጠልም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ተቋሙ ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነት፣ ከብሄርና የሃይማኖት ልዩነቶች ነፃ እንዲሆን የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ተመራቂዎቹ ሁሉንም እንዲያገለግሉና የኢትዮጵያን የደህንነት ዋስትና ለማረጋገጥ ጠንክረው እንዲሰሩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሳስበዋል።

 

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው የደህንነት መኮንኖቹ ስልጠና የብሄራዊ ደህንነትና መረጃ ማዕከል፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲና የአገር መከላከያ ሰራዊት የደህንነት አገልግሎት ማሻሻያዎችን ተከትሎ የተሰጠ ነው።

leave a reply