Breaking News

ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በገቢዎች ሚኒስቴር ቅርንጫፍ የድንገቴ ጉብኝት አደረጉ

ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በገቢዎች ሚኒስቴር ቅርንጫፍ የድንገቴ ጉብኝት አደረጉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የድንገቴ ጉብኝታቸውን በመቀጠል በፌዴራል የመካከለኛ ገቢ ግብር ከፋዮች ቢሮ በመጎብኘት ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ከቢሮው ሰራተኞች ጋር እንዲሁም ግብር ለመክፈል እየተጠባበቁ ከነበሩ ግብር ከፋዮች ጋር ተገናኝተዋል።

ከሳምንት በፊት ከሚኒስትር መስሪያ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር የአፈጻጸም ግምገማዎች በተካሄደበት ወቅት እንደተገለፀው የመንግስት ተቋማትና ሰራተኞች የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ መሆኑን ለማረጋገጥ ይህን መሰል ድንገቴ ጉብኝቶች እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጻቸው ይታወሳል ብሏል የገቢዎች ሚኒስቴር ።

leave a reply