Breaking News

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሲጋራ ማጨሻ ስፍራን የሚገድብና አልኮልን በብሮካስት መገናኛ ብዙሃን ማስተዋወቅን የሚከለክል አዋጅ አፀደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሲጋራ ማጨሻ ስፍራን የሚገድብና አልኮልን በብሮካስት መገናኛ ብዙሃን ማስተዋወቅን የሚከለክል አዋጅ አፀደቀ።

ምክር ቤቱ አዋጁን ያጸደቀው በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ስብሰባው ነው ።

በፀደቀው አዋጅ መሰረት  በመስሪያ ቤቶች፣ በጤና ተቋማት እና የወጣቶች መዝናኛዎች በሚገኙባቸው አከባቢዎች 100 ሜትር ርቀት ውስጥ ሲጋራ ማጨስ ክልክል መሆኑ ተደንግጓል።

ከዚህ በተጨማሪም አዋጁ ማንኛውንም የአልኮል ምርት በብሮድካስት ሚድያ ማስተዋወቅን ከልክሏል።

 

ከዚህ ቀደም በአዋጁ ላይ ውይይት በማድረግ ሂደት ላይ ከምሽቱ 5 ሰዓት እስከንጋቱ 12 ሰዓት የአልኮል መጠጥን ለማስተዋወቅ እንዲቻል በሚል አዋጁ ተሻሽሎ ቀርቦ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

 

ነገር ግን አብዛኞቹ የምክር ቤት አባላት ግን ይህንን በመቃወም በብሮድካስት የአልኮል ማስታወቂያ ጭራሽ መተላለፍ የለበትም የሚል ሃሳብ በማቅረባቸው አዋጁ የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያ ሙሉ በሙሉ በብሮድካስት ሚዲያ እንዳይተላለፍ የሚል ድንጋጌ በማካተት ክልከላ አደርጓል።

 

በአዋጁ መሰረት ከ21 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች አልኮል መሸጥ ክልክል መሆኑም ተገልጿል።

 

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብም ተወያቶ አፅድቆታል።

leave a reply