EthiopiaPolitics

ጠ/ሚር አብይ አሕመድ በዛሬው እለት በጽ/ቤታቸው የጊኒ ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴንና ልዑካቸውን ተቀብለው አነጋገሩ።

ጠ/ሚር አብይ አሕመድ በዛሬው እለት በጽ/ቤታቸው የጊኒ ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴንና ልዑካቸውን ተቀብለው አነጋገሩ።

በአትዮጵያና በጊኒ መካከል ስላለው መልካም ወዳጅነት የጠቀሱት ጠ/ሚሩ ግንኙነቱን ለማጠናከር መልካም መሰረት እንደሚጥል ጠቅሰዋል።

ፕሬዝዳንት ኮንዴ በበኩላቸው ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በአገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ሂደትን በማምጣና በመምራት ያሳዩትን ለውጥ እንዲሁም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ለረጅም አመታት የነበረውን ቋጠሮ ለመፍታት በመቻላቸው ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል።

ከሁለትዮሹ ውይይት በኋላም ሁለቱ መሪዎች የጥምር ሚኒስቴራዊ ኮሚሽን ምስረታ፣ ግብርና፣ የአየር ትራንስፖርት፣ ጤና፣ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርትና ባህልና ቱሪዝም ዘርፎች ዙሪያ አብሮ ለመስራት በዛ ያሉ ስትራቴጂክ ስምምነቶችን ፈርመዋል ።

ምንጭ ጉዳይ፤- ሚኒስቴር

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button