Breaking News

ግብፅ የጋዳፊን ልጅ ለምርጫ እያዘጋጀች ነው ተባለ፡፡

በዚህ ዓመት መጨረሻ የሚካሄደውን የሊቢያን ምርጫ በቅርበት ትከታተለዋለች፡፡

ግብፅ የጋዳፊን ልጅ ለምርጫ እያዘጋጀች ነው ተባለ፡፡

የፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ መንግስት በፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለመወዳደር በዝግጅት ላይ ያለውን የቀድሞው የሊቢያ ፕሬዝዳንት ሙአመር ጋዳፊ  ልጅ ሳይፍ አል ኢስላም ጋዳፊን በሚስጥር እየደገፈው ነው ተብሏለል፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ግብፅ በዚህ ዓመት መጨረሻ የሚካሄደውን የሊቢያን ምርጫ በቅርበት ትከታተለዋለች፡፡

ይህን የምታደርገውም ከራሷ የፀጥታ ሁኔታ ጋር በማገናኘት ነው፡፡ በመሆኑም ሳይፍ አል ኢስላም በምርጫው ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ እንዲቀርብ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ተዘጋጅታለች ነው የተባለው፡፡

ከአል አህራም የፖለቲካ እና ስትራቴጂ ጥናት ተቋም ተገኘ የተባለ መረጃ እንደሚያሳየው  የአል ኢስላም የቅርብ ሰዎች ካይሮ ውስጥ ከሊቢያ የጎሳ መሪዎች ጋር  ውይይት አድርገዋል፡፡

ውይይቱም በመጭው ምርጫ እጩ ሆኖ የሚቀርበውን አል ኢስላም ደጋፊዎችን እንዴት ማደራጀት ይቻላል በሚለው ጉዳይ ዙሪያ ያተኮረ ነው ፡፡

በግብፅ የደህንነት ሰዎች ድጋፍ ካይሮ ላይ የተከናወነው ውይይት በመጭው ምርጫ ዙሪያ ለመወያየት  በሊቢያ ሲርት ለሚካሄደው ስብሰባ በር ከፋች ነው ተብሏል፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

leave a reply