Breaking News

የገቢዎች ሚኒስቴር በ 6 ወራት ዉስጥ 98 ነጥብ 96 ቢሊየን ብር ሰብስቤያለሁ   አለ፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር በ 6 ወራት ዉስጥ 98 ነጥብ 96 ቢሊየን ብር ሰብስቤያለሁ   አለ፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር በ 6 ወራት ዉስጥ 98 ነጥብ 96 ቢሊየን ብር ሰብስቤያለሁ   አለ፡፡

ሚኒስቴሩ ይህንን ያለዉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 25ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የ2011 በጀት ዓመት የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ነዉ ።
የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤም በምክር ቤቱ ተገኝተው  ሪፖርቱን አቅርበዋል።

ወ/ሮ አዳነች  በሪፖርታቸው፥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት ስድስት ወራት የታክስ ንቅናቄ መድረክ በመፍጠር የተለያዩ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል።
በዚህም የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 6 ወራት 122 ነጥብ 18 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 98 ነጥብ 96 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል።

የገቢ አሰባሰቡም ከእቅዱ አንፃር ሲታይ 80 ነጥብ 76 በመቶ ማከናወን መቻሉም ነው የተገለጸዉ።

ምንጭ ገቢዎች ሚኒስቴር

leave a reply