Regions

ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ የአፍሪካ የከንቲባዎች እና መሪዎች አለም አቀፍ ትብብር ፤ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና አስተባባሪ ሆነው ተመረጡ

በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ የሆነው African Renaissance and Diaspora Network የተባለ ተቋም ኢ/ር ታከለ ኡማን የአፍሪካ የከንቲባዎች እና መሪዎች አለም አቀፍ ትብብር ፤ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና አስተባባሪ አድርጎ መረጠ፡፡

የተቋሙ ፕረዝዳንት ዶ/ር ጂብሪል ዲያሎ ኢ/ር ታከለ ኡማ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየሰሩት ባለው የልማትና መልካም አስተዳደርን የማስፈን ስራዎች እና የጎዳና ላይ ልጆችን በዘላቂነት ለማቋቋም እየሰሩ ባለው ስራ የአፍርካ የከንቲባዎች እና መሪዎች አለምአቀፍ ትብብር የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና አስተባባሪ ( Global Alliance of Mayors and Leaders; East African Chair) አድርጎ መምረጡን አሳውቋል፡፡

ተቋሙ በቀጣይነትም ሃገሪቷ የተያያዘችውን የለውጥ ጉዞ እንደሚደግፍ እና በኢትዮጵያ እና አሜሪካ ያሉ ከፍተኛ የት/ት ተቋማትን በማጣመር ወጣት የከተማዋ ነዋሪዎች የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እንደሚንቀሳቀስም አስታውቋል፡፡የዜናው ምንጭ የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ነው።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button