Breaking News

ለውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

ለውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ስልጠናውን የሰጠው ከፌደራል፣ከክልሎች እና ከከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ 70 የስራ ስምሪት ባለሙያዎች ነው።

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ብርሀኑ አበራ እንደተናገሩት በአሁኑ ጊዜ ለሥራ ወደ ውጭ ሀገር ሄደው መስራት የሚፈልጉ ዜጐች ህግና ሥርዓትን ተከትለው በመሄድ በሚሰሩበት አገር መብታቸው፣ ደህንነታቸውና ክብራቸው ተጠብቆ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ፣አደረጃጀትና የአሠራር ሥርዓት በተሻለ ሁኔታ ተዘርግቷል ፡፡

በዚህ ዙሪያ በወጡ የህግ ማዕቀፎች ላይ የአስፈጻሚና የባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ የማሳደግ ሰፋፊ ስራዎች መሰራታቸውንም ገልጸዋል፡፡

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአውሮፓ ህብረት ጋር ሆኖ በሚያስፈፅመው ይኸው ፕሮጀክት አማካኝነት የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተደራሽ ለማድረግ ያለመ መሆኑንም ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በቅድመ ጉዞ ገለፃ፣ በኢንስፔክሽን እና ከዜጎች የሚቀርቡ አቤቱታዎች ተቀብሎ በማስማማት ረገድ የባለሙያዎች አቅም መገንባት ተቀዳሚ ተግባር አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝም አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል፡፡

 

 

 

leave a reply