SportSports

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ

 

የሊጉ የሳምንቱ መርሀግብር ዛሬ ሲጀመር ዕለቱ በርካታ ግጥሚያዎች ይከናወናሉ፡፡ ቀን 9፡30 የኦሌ ጉናር ሶልሻዬሩ ማንችስተር ዩናይትድ ወደ ለንደን አምርቶ ክሬቭን ኮቴጅ ላይ በክላውዲዮ ራኔዬሪ የሚመራውን ፉልሃም ይገጥማል፤ በቅርብ ጨዋታዎች እየተፈተ ውጤት ይዞ የሚወጣው ዩናይትድ በለንደኑ ቡድንም ሊፈተን እንደሚችል ተነግሯል፡፡

ምሽት 12፡00 በተመሳሳይ አምስት ጨዋታዎች ሲደረጉ፤ የሊጉን መሪነት ለማንችስተር ሲቲ ያስረከበው ሊቨርፑል አንፊልድ ላይ ከቦርንመዝ ይጫወታል፤ ጫና ውስጥ የሚገኘው የየርገን ክሎፕ ቡድን፤ በዚህም በኤዲ ሃው ታክቲክ ሊንገራገጭ እንደሚችል ተንታኞች እየተናገሩ ነው፡፡

የኡናይ ኢምሪው አርሰናል ደግሞ ወደ ጆን ስሚዝ ስታዲየም አቅንቶ የሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘውን ሀደርስፊልድ ታውን ይገጥማል፡፡

በሌሎች ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ በሴል ኽረስት ፓርክ ስታዲየም ከዌስት ሃም፣ ሴንት ሜሪ ላይ ሳውዛምፕተን ከ ካርዲፍ እና ዋትፎርድ በቪካሬጅ ከኢቨርተን ሲገናኙ፤ ምሽት 2፡30 ደግሞ ብራይተን በአሜክስ ከበርንሊ ይፋለማሉ፡፡

በነገው ዕለት ሁለት ጨዋታዎች ሲደረጉ የሳምንቱ ተጠባቂ ግጥሚያ ኢቲሃድ ላይ በማንችስተር ሲቲ እና ቼልሲ መካከል ይከናወናል፤ ሲቲ የውድድር ዓመቱ ያለመሸነፍ ጉዞው የመጀመሪያ ሽንፈት አሀዱ ያለው የማውሪዚዮ ሳሪው ቡድን ሲሆን በዚህም ጨዋታ ፈታኝ ፍልሚያ ምሽት 1፡00 ሲል ያከናውናሉ፡፡

በዕለቱ አስቀድሞ ቀን 10፡30 ቶተንሃም ሆትስፐር በዌምብሌይ ከሌስተር ሲቲ ይገናኛል፤ ሰኞ በሊጉ የሳምንቱ ማሳረጊያ ግጥሚያ ወልቭስ ከኒውካስትል ዩናይትድ ምሽት 5፡00 ላይ ይጫወታሉ፡፡

ሲቲ በ26 ጨዋታዎች በሰበሰባቸው 62 ነጥቦች የሊጉ አናት ላይ ተሰይሟል፤ በ25 ግጥሚያዎች ተመሳሳይ 62 ነጥቦችን ያከማቸው ሊቨርፑል በግብ ክፍያ አንሶ ሁለተኛ ሲሆን ቶተንሃም በ57 ሶስተኛ፣ ቼልሲ በ50 አራተኛ እንዲሁም ማንችስተር ዩናይትድ እና አርሰናል በ48 እና 47 ነጥቦች አምስተኛ እና ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

የሊቨርፑሉ መሀመድ ሳላህ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን በ16 ግቦች እየመራ ነው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button