EconomyEthiopia

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም በጉዞና ቱሪዝም ዘርፍ የ2019 ተሸላሚ ሆኑ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም በጉዞና ቱሪዝም ዘርፍ የ2019 ተሸላሚ ሆኑ፡፡

በየዓመቱ በተለየዩ ዘርፎች ተጽእኖ ፈጣሪ አፍሪካውያንን እየመረጠ የሚሸልመው ሞስት ኢንፍሉኤንሻል ፒፕል ኦፍ አፍሪካን ዲሰንት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም በጉዞና ቱሪዝም ዘርፍ የ2019 ተሸላሚ አድርጓቸዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው ሽልማቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ዓመታት ያስመዘገበው አንጸባራቂ ስኬት መሆኑን ተናግረው፤ ይህም የአየር መንገዱ ማኔጅመንት እና መላው ሰራተኞች ትጋት የተገኘ ነው ብለዋል፡፡

ከአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን በተካሄደው በዚህ የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት  በአሜሪካ የአፍሪካ ህብረት አምባሳደር ዶ/ር አሪካና ቺሆምቦሪ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬት ትልቅ ኩራት እንደተሰማቸው ተናግረዋል፡፡

የሞስት ኢንፍሉኤንሻል ፒፕል ኦፍ አፍሪካን ዲሴንት ዋና ስራ አስኪያጅ ካሚል ኦሉፎዎቢ በስራቸው መልካም ተጽእኖ ያሳደሩ አፍሪካውያንን በመሸለም ሌሎቸን ማነቃቃት የሽልማቱ ዓላማ ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይም በየዓመቱ  ከአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ጎን ለጎን በተለያዩ ዘርፎች የሽልማት ስነ ስርዓት እንደሚካሄድ ተነግሯል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close