Ethiopia

ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ምን አሉ…?

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 03፣ 2014  አሸባሪው ህወሓት ለኢትዮጵያ ደህንነት አደጋ በማይሆንበት ደረጃ እስኪደርስ ይመታል ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ። ጄኔራል ብርሃኑ አሸባሪው ህወሓት የአማራንና የአፋርን መሬት ይዞ እንዲኖር የሚፈልግና የሚወስን መንግሥት የለም ብለዋል። መከላከያ ሰራዊትም ከዚህ የተለየ አቋም የለውም ሲሉ ገልፀዋል። የአማራንና የአፋርን አንዳንድ ወረዳዎችን የማስለቀቅ፤ እንዲሁም በክልሎቹ የገባው ኃይል ሁለተኛ ዝር እንዳይልና ለኢትዮጵያም ስጋት በማይሆን ደረጃ ይመታል ብለዋል።

ስለ አሸባሪው ህወሓት ስናስብ ከአማራ መሬት የማስወጣትን ሃሳብ አይደለም የምናስበው። ያሰመርነው መስመርም የለም። አሸባሪ ቡድኑ ለአገሪቱ ህልውና አደጋ በማይሆንበትና የውጭ ቅጥረኞች ገዝቶ ለኢትዮጵያ መፍረስ በማይሰራበት ሁኔታ መመታት አለበት ሲሉ አስታውቀዋል። በአገርም ላይ የህልውና አደጋ የደቀነው ወያኔ ነው እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ሕዝብ ላይ የደቀነው የህልውና አደጋ የለም ያሉት ጄኔራል ብርሃኑ፤ ከትግራይ ለቅቀን ስንወጣ ያደረገውን አይተናል ብለዋል። አሸባሪ ቡድኑ በትግራይ መብራት አጥፍቶ፣ የግንኙነት መስመሩን አቋርጦ፣ ሕዝቡ ርዳታ እንዳያገኝ ከልክሎ፣ ህጻናትን አስገድዶ በጦርነት አሰልፎ ሲያስፈጅ መቆየቱን አስታውሰዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button