Breaking News

የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይጀመራሉ

ኔይማር እና ኢዲንሰን ካቫኒ እንዲሁም ቶማስ ሙኒዬ በምሽቱ ጨዋታ እንደማይኖሩ በአሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል በኩል ተረጋግጧል፡፡

የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይጀመራሉ

 

የ2018/19 የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ በ16ቱ ክለቦች መካከል የሚከናወነው የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች፤ ዛሬ ምሽት በሚከናወኑ ሁለት ግጥሚያዎች ይጀመራል፡፡

የፈረንሳዩ ፒ.ኤስ.ጂ ወደ እንግሊዝ በማምራት ኦልድ ትራፎርድ ላይ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ይፋለማል፡፡

በፓሪሱ ቡድን በኩል ቁልፍ ተጫዋቾቹ ኔይማር እና ኢዲንሰን ካቫኒ እንዲሁም ቶማስ ሙኒዬ በምሽቱ ጨዋታ እንደማይኖሩ በአሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል በኩል ተረጋግጧል፡፡

ይሁን እንጂ ማርኮ ቬራቲ ለጨዋታው ዝግጁ እንደሆነ ተነግሯል፤ ከክልያን ምባፔም ጋር አንሄል ዲማሪያ እና ድራክስለር ሊጣመሩ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡

በኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ቡድን በኩል ጉዳት ላይ ከሚገኙት አንቶኒዮ ቫሌንሲያ እና ማቲዎ ዳርሚያን ውጭ ሙሉ ቡድኑ ዝግጁ ነው፡፡ በፉልሃሙ የሊግ ግጥሚያ ያልተሰለፉት ማርከስ ራሽፈርድ፣ አሌክሲስ ሳንቼዝ እና ጄሴ ሊንጋራድ የመጀመሪያው አሰላለፍ ውስጥ ይጠበቃሉ፡፡ ጨዋታው ምሽት 5፡00 ላይ ይከናወናል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት ሌላኛው ግጥሚያ ጣሊያን ምድር ላይ በሮማ እና ፖርቶ መካከል ስታዲዮ ኦሎምፒኮ ላይ ይካሄዳል፡፡

የሮማው ኮስታስ ማኖላስ ከጉዳት ሲመለስ ፓትሪክ ሽክ በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጭ እንደሆነ ተነግሯል፤ የሮቢን ኦልሰን ጉዳይም አጠራጣሪ ሁኗል፡፡

በፖርቱጋሉ ፖርቶ ወገን ግብ አስቆጣሪያቸው ሙሳ ማሬጋ በጉዳት ከምሽቱ ጨዋታ ውጭ ሲሆን ጀሱስ ኮሮና በቅጣት አይሰለፍም፡፡

leave a reply