Breaking News

የኢሮፓ ሊግ የመጨረሻ 32ቱ ቡድኖች የጥሎ ማለፍ በርካታ ጨዋታዎች ዛሬ ይደርጋሉ

በኢሮፓ ሊግ በዛሬው ምሽት በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ወደ 15 ያህል ፍልሚያዎች ይካሄዳሉ፡፡

የኢሮፓ ሊግ የመጨረሻ 32ቱ ቡድኖች የጥሎ ማለፍ በርካታ ጨዋታዎች ዛሬ ይደርጋሉ

በኢሮፓ ሊግ በዚህ ዙር 16 ያህል ግጥሚያዎች የሚካሄዱ ሲሆን በዛሬው ምሽት በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ወደ 15 ያህል ፍልሚያዎች ይካሄዳሉ፡፡

 

በዙሩ ከሚካሄዱ የመጀመሪያ ግጥሚያዎች መካከል ከትናንት በስቲያ ቱርክ ላይ ፌነርባቼ በእስላም ስሊማኒ ብቸኛ ግብ ዜኒት ፒተርስበርግን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

 

ዛሬ ምሽት የሚከናወኑት ጨዋታዎች ምሽት 2፡55 ላይ በተመሳሰይ ስምንት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፤ ቀሪዎቹ ሰባት ግጥሚያዎች ደግሞ ምሽት 5፡00 ላይ ይከናወናሉ፡፡

 

ምሽት 2፡55 ላይ ከሚከናወኑት መካከል፤ የሰሜን ለንደኑ አርሰናል ወደ ቤላሩሷ ባሪሳው ከተማ አቅንቶ ከባቴ ቦሪሶቭ ጋር ቦሪሶቭ አሬና ላይ ይጫወታል፡፡

 

በምሽቱ መድፈኞቹ ሜሱት ኦዚል እና አሮን ራምሴን ከስብስቡ ውጭ እንዳደረጉ ተነግሯል፡፡

 

በአሰልጣኝ አርሴን ቪንገር ዘመን የመድፈኞቹ አባል የነበረው አሌክሳንደር ኸሌብ፤ የቀድሞ ክለቡን ይገጥማል፡፡

 

ከተጠባቂ ጨዋታዎች መካከል ላትሲዮ  በስታዲዮ ኦሊምፒኮ ከሲቪያ ይፋለማል፤ ኢንተር ሚላን ወደ ኦስትሪያ አምርቶ ከራፒድ ቬና ሲጫወት፤ ጋላታሳራይ ከቤንፊካ፣ ክራስኖዳር ከ ባየር ሊቨርኩሰን፤ ኦለምፒያኮስ ከ ዳይናሞ ኬቭ፣ ሬን ከ ሪያል ቤቲስ፣ ስላቪያ ፕራህ ከ ሄንክ ይጫወታሉ፡፡

 

ምሽት 5፡00 ላይ ደግሞ አስደንጋጭ ሽንፈቶች እየገጠመው የሚገኘው የማውሪዚዮ ሳሪው ቼልሲ ስዊድን ላይ ከማልሞ ጋር በማልሞ ኒው ስታዲየም ይፋለማል፡፡

 

ማርኮስ አሎንሶ እና ሩበን ሎፍተስ- ቺክ በዛሬው ግጥሚያ ሊኖሩ እንደማችሉ ተጠቁሟል፡፡

 

በተመሳሳይ ሰዓት ሴልቲክ ከ ቫሌንሲያ፣ ክለብ ብሩዥ ከ ሬድ ቡል ሳልዝበርግ፣ ሻክታር ዶኔስክ ከ አይንትራክት ፍራንክፉርት፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን ከ ቪያሪያል፣ ቪክቶሪያ ፕለዘን ከ ዲናሞ ዛግሪብ እንዲሁም ዙሪክ ከ ናፖሊ ይገናኛሉ፡፡

 

leave a reply