Breaking News

በኢሮፓ ሊግ አርሰናል ከሜዳው ውጭ በጠባብ ውጤት ሲሸነፍ፤ ቼልሲ ድል አድርጓል

አርሰናል በባቴ ቦሪሶቭ የ1 ለ 0 ሽንፈት ገጥሞታል፡፡

በኢሮፓ ሊግ አርሰናል ከሜዳው ውጭ በጠባብ ውጤት ሲሸነፍ፤ ቼልሲ ድል አድርጓል

 

 

የኢሮፓ ሊግ በ32 ቡድኖች መካከል የሚካሄደው የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ግጥሚያዎች ትናንት ምሽት ተካሂደዋል፡፡ በምሽቱ የተከናወኑት 15 ግጥሚያዎች በሁለት የተለያዩ ሰዓቶች ተደርገዋል፡፡

 

ምሽት 2፡55 ላይ ስምንት ፍልሚያዎች ሲካሄዱ፤ ወደ ቤላሩስ ያመራው የእንግሊዙ አርሰናል በባቴ ቦሪሶቭ የ1 ለ 0 ሽንፈት ገጥሞታል፡፡ ለባለሜዳዎቹ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ የመጀመሪያው የጨወታ አጋማሽ ከመጠናቀቁ ጥቂት ሰከንዶች በፊት ከስታሴቪች የተሻገረችውን የቅጣት ምት ኳስ ስታኒስላቭ ድራገን በጭንቅላት በመግጨት አስቆጥሯል፡፡

 

ባቴዎች ማሸነፋቸውን ተከትሎ በሜዳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የእንግሊዝን ክለብ  ላይ ድልን ተቀዳጅተዋል፡፡

 

ፈረንሳያዊው አሌክሳንደር ላካዜት በ85ኛው ደቂቃ ላይ የባቴውን ተጫዋች አሌክሳንደር ፊሊፖቪች በክርን በመማታቱ የቀይ ካርድ ሰለባ ሁኗል፡፡

 

በቀይ ካርድ ከሜዳ የተሰናበተው ላካዜት ላልተገባ ድርጊቱ ቡድኑንና ደጋፊዎቹን ይቅርታ ጠይቆ በኤምሬቱ ጨዋታ እርሱ እንኳ ባይኖር አጋሮቹ እንደማያሳፍሩት ተናግሯል፡፡

 

ምሽት 5፡00 ላይ ደግሞ ቼልሲ ወደ ስዊድን አቅንቶ ማልሞን 2 ለ 1 ረትቶ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል፡፡ ሮዝ ባርክሌይ እና ኦሊቪዬ ጂሩ ለሰማያዊዎቹ ድል አድራጊነት ግብ በማስቆጠር ለማውሪዚዮ ሳሪ እፎይታን ሰጥተዋል፡፡ አንደርስ ክሪስቲያንሰን ማልሞን ከባዶ መሸነፍ ያዳነች ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ጂሩ ደግሞ የጨዋታው ኮከብ ተብሏል፡፡

 

 

በሌሎች ጨዋታዎች በስታዲዮ ኦሊምፒኮ  ላትሲዮ 0 ለ 1 ሲቪያ፣ ራፒድ ቬና 0 ለ 1 ኢንተር ሚላን፤ ጋላታሳራይን 1 ለ 2 ቤንፊካ፣ ኦለምፒያኮስ 2 ለ 2 ዳይናሞ ኬቭ፣ ሬን 3 ለ 3 ሪያል ቤቲስ፣  ቫሌንሲያ 2 ለ 0 ሴልቲክ፣ ክለብ ብሩዥ 2 ለ 1 ሬድ ቡል ሳልዝበርግ፣ ዙሪክ 1 ለ 3 ናፖሊ፣ ቪክቶሪያ ፕለዘን 2 ለ 1 ዲናሞ ዛግሪብ፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን 0 ለ 1፣ ሻክታር ዶኔስክ 2 ለ 2 አይንትራክት ፍራንክፉርት፣ እና ክራስኖዳር 0 ለ 0 ባየር ሊቨርኩሰን ተለያይተዋል፡፡

 

 

leave a reply