Breaking News

የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

የኤርትራ የባህል እና የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አዲስ አበባ ገባ

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ አንደሚጠቁመው ከ60 በላይ አባላት ያሉትና ታዋቂው አርቲስት በረኸት መንግስተአብን ጨምሮ የተለያዩ አከላትን ያካተተ የኤርትራ የባህልና የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል።

ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማሪፊያ ሲደርስ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ከአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በተወከሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል።

የባህል ቡድኑ በቆይታው በኢትየጵያ የተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር የተለያዩ የባህል ዝግጅቶችን በማቅረብ የሁለቱን አገሮች የህብ ለህዝብ ትስስር የማጠናከር ስራ ይሰራል ሲል የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ገልፃል።

 

leave a reply