Economy

የመንገድ ፈንድ ጽህፈት ቤት ባለፉት ሰባት ወራት 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ

የመንገድ ፈንድ ጽህፈት ቤት ባለፉት ሰባት ወራት 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡ገቢው ለመንገድ ጥገናና ለመንገድ ደህንነት እርምጃዎች ማስፈጸሚያ ይውላል ብሏል።

ጽህፈት ቤቱ ለአርትስ ቲቪ የላከው የተቋሙ የ2011 በጀት አመት የሰባት ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያመለክተው በሰባት ወራት የስራ አፈጻጸሙ  1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ችሏል።

በዚህም የእቅዱን 92 በመቶ ማሳካት ችሏል ብሏልችሏል ብሏል

ጽፈት ቤቱ ገቢውን የሰበሰበው በነዳጅ ላይ ከተጣለ ታሪፍ፣ ከተሸከርካሪ ዘይትና ቅባት ፣ከመንገድ መጠቀሚያ ክፍያ፣ ከግምጃ ቤት ሰነድ ግዢ ወለድ እና ከዓመታዊ የተሸከርካሪ ፈቃድ እድሳት መሆኑም ተነግሯል፡፡

ከተሰበሰበው ገቢ ላይ በፈንዱ የሚደገፉ የመንገድ ጥገና ፕሮጀክቶች በሚያቀርቡት የክፍያ ሰርተፊኬት መሰረት 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ለመክፈል ታቅዶ 655 ሚሊዮን ብር ክፍያ ተፈጽሟል ብሏል።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ፣ ዘጠኝ ክልሎች እና አዲስ አበባን ጨምሮ የክልልና የዞን ከተሞች በፈንዱ ክፍያ ከተፈጸመላቸው መካከል ናቸው፡፡

ባለፉት 7 ወራት ከሰባት ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ጥገና መከናወኑንም የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button