Uncategorized

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው  በቤኒሻንጉልና ጋምቤላ ትምህርት ቤቶችን ሊያስገነቡ ነው

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው  በቤኒሻንጉልና ጋምቤላ ትምህርት ቤቶችን ሊያስገነቡ ነው

 

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ በሁለቱ ክልሎች  20 ሚሊዮን ብር ትምህርት ቤቶቹን ለማስገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ከሁለቱም ክልሎች ትምህርት ቢሮ ተወካዮች ጋር ተፈራርመዋል።

 

እንደ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ገለፃ ለዜጎች ጥራት ያለው ትምህርት ፍትሃዊ በሆነ ሁኔታ ተደራሽማድረግ የሀገሪቱን የወደፊት ትውልድ ለማነጽ እና ለማዘጋጀት ቁልፍ ተግባር ነው ።

 

በተያያዘ ዜናም ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የተለያዩ የውጭ ሀገር ተቋማትን በማስተባበር ያሰባሰቧቸውን የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶች የህፃናት አልጋዎች፣የደም ማስቀመጫ ፍሪጆች  እና ተሽከርካሪ የሆስፒታል ወንበሮች

ለሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አስረክበዋል።

የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ለአርትስ ቲቪ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው  የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት  በገጠር አካባቢ በትምህርት ቤት ርቀት ምክንያት ትምህርት የሚያቋርጡ ተማሪዎችን ችግር ለመቅረፍ ባቅራቢያቸው ትምህርት ቤቶቹን እንደሚገነባ ገልጿል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button