EthiopiaSocial

ቀደምት አያታችን ሉሲ አፍሪካን እየዞረች ስለሰላም ልትስብክ ነዉ፡፡

ቀደምት አያታችን ሉሲ አፍሪካን እየዞረች ስለሰላም ልትስብክ ነዉ፡፡

ጉዞዋም  “ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር” ተብሎ ተሰይሟል፡፡

ሉሲ(ድንቅነሽ)  በጉዞዋ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት በመባል በሚታወቁት ኢትዮጵያ፤ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ሱማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ሪፐብሊክ እንዲሁም ኬንያና ኡጋንዳ ሀገራትን ያቀፈ የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የሚያስተሳስራቸው ሀገራትን ያካተተ ነዉ፡፡

“ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር” የሁሉም ኢትዮጵያዊ እናት በሆነችው ሉሲ(ድንቅነሽ) አማካኝነት የሰላምና የፍቅር መልዕክቶች በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ስለፍቅር ስለ ህዝቦች አንድነትና የጋራ ተጠቃሚነት እንዲሁም ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚረዱ መልዕክቶች የሚተላለፉበት የጉዞ ፕሮግራም  ነው፡፡

የሉሲ ጉዞ ፕሮግራምም ሀሙስ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎችና ሌሎች ተጋባዥ ዕንግዶች በተገኙበት ይካሄዳል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button