SportSports

በዩሮፓ ሊግ አርሰናል ሲያሸንፍ ቼልሲ ከሜዳው ውጭ ነጥብ ተጋርቷል፡፡

የዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት ተካሂደዋል፡፡

እንግሊዝ ምድር ላይ አርሰናል ኤመሬትስ ላይ የስፔኑን ቡድን ቫሌንሲያ አስተናግዶ ከመመራት ተነስቶ ጨዋታውን በ3 ለ 1 ውጤት አሸናፊ ሁኗል፡፡

እንግዳው ቫሌንሲያ ጎል ለማስቆጠር በጨዋታው ጅማሮ ላይ እንቅስቃሴዎችን ያደረገ ሲሆን ተሳክቶለት ፈረንሳያዊው ሙክታር ዲያካቢ በ11ኛው ደቂቃ በጭንቅላቱ የገጫት ኳስ ፒተር ቼክ መረብ ላይ አርፋለች፡፡

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ግን መድፈኞቹ የአቻነት ግብ አግኝተዋል፤ ኦባማያንግ ለአሌክሳንደር ላካዜት ያቀበላትን ኳስ ከመረብ ተዋህዳለች፡፡

የመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ላይ ከግራኒት ዣካ የተሻገረችውን ኳስ ላካዜት በማስቆጠር ለራሱ እና ለቡድኑ ሁለተኛውን ግብ አሳክቷል፡፡  

ጋቦናዊው ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ የጨዋታው መደበኛ ጊዜ መጠናቀቂያ ላይ ከላካዜት በኩል ያገኛትን ኳስ በአግባቡ ተጠቅሞ አርሰናል በስፔኑ ቡድን ላይ በሁለት የግብ ልዩነት ድል እንዲቀዳጅ አድርጓል፡፡

በሌላኛው ጨዋታ ቼልሲ ወደ ጀርመን አምርቶ ኮሜርዝ ባንክ አሬና ላይ ከጀርመኑ አይንትራክት ፍራንክፉርት ጋር ተጫውቶ ነጥብ ተጋርቷል፡፡

ጨዋታው በአንድ አቻ ውጤት ሲጠናቀቅ ባለሜዳው ቡድን 23ኛው ደቂቃ ላይ በሰርቢያዊው ሉካ ዮቪች አማካኝነት ቀዳሚ ሁኗል፤ ኤደን ሃዛርድን በመጀመሪያው አሰላለፍ ወደ ሜዳ ይዘው ያልገቡት ሰማያዊዎቹ የመጀመሪያው አጋማሽ ከመጠናቀቁ በፊት በስፔናዊው ፔድሮ ሮድርጊዩዝ ጎል አቻ ሁነዋል፡፡

ቼልሲ በምሽቱ አቻ መሆኑን ተከትሎ በ16 የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ያለሽንፈት በመጓዝ የመጀመሪያው ቡድን ሆኗል፤ የስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ በ2011/12 የውድድር ዓመት ይዞት የነበረውን ያመሸነፍ ክብረወሰን ማሻሻል ችሏል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button