AfricaPolitics

46ኛው የ(ኢጋድ) ስብሰባ በቀይ ባህርና በባህረ ሰላጤው አካባቢ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ዉሳኔዎች ያሳለፈበት ነዉ ተባለ፡፡

46ኛው የ(ኢጋድ) ስብሰባ በቀይ ባህርና በባህረ ሰላጤው አካባቢ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ዉሳኔዎች ያሳለፈበት ነዉ ተባለ፡፡

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ሰብሳቢነት በጅቡቲ ለሁለት ቀናት  በተካሄደው 46ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ)የሚኒስትሮች ካውንስል ስብሰባ ፤ዉጤታማ ዉሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል፡፡

የኢጋድን አሰራር ለማዘመን የቀረበውን የማሻሻያ ሃሳብ አስፈላጊነት ውይይት በማድረግ እስከ ቀጣዩ የ(ኢጋድ) መደበኛ ስብሰባ ድረስ በሚመለከተው አካል በኩል ተጨማሪ ውይይት እንዲደረግበትና ለቀጣይ ውሳኔ እንዲቀርብ ወስኗል።

ስብሰባው በተጨማሪም በቀይ ባህርና በባህረ ሰላጤው አካባቢ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ቀጠናዊ አሰራር ለመዘርጋት ከአፍሪካ ህብረትና ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ትብብር መፍጠር በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያም ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን ሰጥቷል።

በስብሳባው የኢጋድ አባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንዲሁም የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ የሌሎች ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ተወካዮች ተገኝተዋል።

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button