EthiopiaSportSports

ከ23 ዓመት በታች የኦሊምፒክ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ለ33 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረበ

23 ዓመት በታች የኦሊምፒክ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ለ33 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረበ

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች የኦሊምፒክ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን በመጋቢት 12 ቀን 2011 ዓ.ም ከማሊ አቻው ጋር ላለበት ጨዋታ 33 ተጫዋቾች በዕጩነት የተመረጡ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

ተጫዋቾቹ የካቲት 26/2011 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚገኘው የቴክኒክና ልማት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ተገልፆላቸዋል ተብሏል፡፡

በዚህም ከግብ ጠባቂዎች፡- ምንተስኖት አሎ (ባህር ዳር ከተማ)፤ ተክለማርያም ሻንቆ (ሀዋሳ ከተማ)፤ ጆርጅ ደስታ (ኢትዮጵያ መድን)

ተከላካዮች፡- ፈቱዲን ጀማል (ሲዳማ ቡና)፤ሳሙኤል ተስፋዬ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፤ ሸዊት ዮሐንስ (ስሑል ሽረ)፤ ይበልጣል ሽባባው (ኢኮስኮ)፤ አብርሀም ሁሴን (ኤሌክትሪክ)፤ ጌቱ ኃይለማርያም (ሰበታ ከተማ)፤  እንየው ካሳሁን (ወልዋሎ)፤ ደስታ ደሙ (ወልዋሎ)፤ ደስታ ዮሐንስ (ሀዋሳ ከተማ)፤ ዜናው ፈረደ (ባህርዳር ከተማ)፤ ዳዊት ወርቁ (ደደቢት)

አማካዮች፡- ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ)፤ ሐብታሙ ተከስተ (ፋሲል ከነማ) ፤አብዱልከሪም ወርቁ (ወልቂጤ ከተማ)፤ ቴዎድሮስ ታፈሰ (መከላከያ)፤ በረከት ደስታ (አዳማ ከተማ)፤ ከነአን ማርክነህ (አዳማ ከተማ)፤ አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና)፤ አብስራ ተስፋዬ (ደደቢት)፤ አፈወርቅ ሀይሉ (ወልዋሎ)፤ ሰለሞን ወዴሳ (መድን)፤ወንድሜነህ ደረጀ (ባህርዳር)

አጥቂዎች፡ እዮብ ዓለማየሁ (ወላይታ ድቻ)፤ ስንታየሁ መንግስቱ (አርባምንጭ)፤ አማኑኤል ገብረሚካኤል (መቐለ 70 እንደርታ)፤ ያሬድ ከበደ (መቐለ 70 እንደርታ)፤ ፍቃዱ ዓለሙ (መከላከያ)፤ አቡበከር ናስር (ኢትዮጵያ ቡና)፤ ሐብታሙ ገዛኸኝ (ሲዳማ ቡና)፤ እስራኤል እሸቱ (ሀዋሳ ከተማ)፡፡

ከ33ቱ ተጫዋቾች 23ቱ ተመርጠው ለጨዋታ ዝግጁ የሚሆኑ ይሆናል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button